የሶማሊያ ችግርና የአፍሪቃ ሕብረት | ኢትዮጵያ | DW | 15.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሶማሊያ ችግርና የአፍሪቃ ሕብረት

የአፍሪቃ ሕብረት በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የተለያዩ ወገኖች የተለያየ ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ለዉጤት አለመብቃቱን በግልፅ አምኗል።

default

የአፍሪቃ ሕብረት ጦር በሞቃዲሾ

ከዜናዉ እንደ ተከታተላችሁት የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሟል። ይሁንና የአፍሪቃ ሕብረት በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የተለያዩ ወገኖች የተለያየ ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ለዉጤት አለመብቃቱን በግልፅ አምኗል።የሕብረቱ የሠላምና ደሕንነት ምክር ቤት ዛሬ ለምሥራቅ አፍሪቃ፥ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ለአዉሮጳ ሕብረትና ለዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች እንዳስረዳዉ ሶማሊያ በአማፂያንና በመንግሥት ሐይላት ከሚካሄደዉ ዉጊያ በተጨማሪ በመንግሥት ባለሥልጣናት መካካል ያለዉ አለመግባባትም ክፉኛ እየጎዳት ነዉ።

ታደሠ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic