የሶማሊያ ቀዉስ ፤ ኬንያና ተመድ | ኢትዮጵያ | DW | 24.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሶማሊያ ቀዉስ ፤ ኬንያና ተመድ

ሞቃዲሾ የሠፈረዉን የአፍሪቃ ሕብረት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማጠናከር ኢትዮጵያ ሠራዊት ማዋጣት-አለማዋጣትዋ የሚወሰነዉ ነገ-በሚሰየመዉ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ነዉ።

default

የኬንያ ጦር ደ/ሶማሊያ


ኬንያ ደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት ያዘመችዉ ጦሯ በሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አ-ሸባብ ላይ የከፈተዉን ጥቃት እንደሚቀጥል በአዲስ አበባ የኬንያዋ አምባሳደር አስታወቁ።አምባሳደር ዶክተር ሞኒካ ኬ ጁማ እንዳሉት ኢትዮጵያ የኬንያ ጦርን የሚረዳ ጦር ሥለማዝመት-አለማዝመቷ ግን ግልፅ ማብራሪ መስጠት አልፈቀዱም።ይሑንና አምባሳደሯ እንዳሉት ሞቃዲሾ የሠፈረዉን የአፍሪቃ ሕብረት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማጠናከር ኢትዮጵያ ሠራዊት ማዋጣት-አለማዋጣትዋ የሚወሰነዉ ነገ-በሚሰየመዉ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ነዉ።በነገዉ ስብሰባ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ የሚገኙት የሶማሊያ የሽግግር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሸሪፍ ሐሰን ሼኽ አደም ዛሬ ከኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ከአቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተወያይተዋል።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

የሶማሊያ ሰብዓዊ ቀዉስና ጦርነቱ

ሶማሊያ ዉስጥ የሚካሄድ ዉጊያ በቋፍ የሚገኘዉን ሰብዓዊ ቀዉስ እንደሚያባብስ የተመ የሰብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት አመለከተ። የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደሶማሊያ ዘልቀዉ ገብተዋል መባሉን የጠቀሰዉ የአዣንስ ፍራን ፕረስ ዘገባ፤ የሰብዓዊ ርዳታ አስተባባሪዉ ተቋም እንዲህ ያለዉ ጣልቃገብነት ችግሩን ከማባባስ የዘለለ ፋይዳ የለዉም ማለቱን አስታዉቋል። ሸዋዬ ለገሠ ናይሮቢ የሚገኙትን በተመ የሰብዓዊ ርዳታ ጽህፈት ቤት የሶማሊያ አስተባባሪ ማርክ ቦደንን በማነጋገር ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዮ ለገሰ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic