የሶማሊያ ሕገ መንግሥት መፅደቁ | አፍሪቃ | DW | 02.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሶማሊያ ሕገ መንግሥት መፅደቁ

የሶማሊያ ሕገ መንግሥት አፅዳቂ ሸንጎ ትናንት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት በከፍተኛ አፀደቀ። 825 የጎሣ ሽማግሌዎች የተሳተፉበት ሸንጎ በረቂቁ ሕገ መንግሥት ላይ የአንድ ሣምንት ክርክር ካካሄደ በኋላ 621 አባላት ረቂቁን ሕገ መንግሥት ሲደግፉ፡ 13 ተቃውመውታል፤ 11 ደግሞ ድምፅ ከመስጠት ታቅበዋል።

የሶማሊያ ሕገ መንግሥት አፅዳቂ ሸንጎ ትናንት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት በከፍተኛ አፀደቀ። 825 የጎሣ ሽማግሌዎች የተሳተፉበት ሸንጎ በረቂቁ ሕገ መንግሥት ላይ የአንድ ሣምንት ክርክር ካካሄደ በኋላ 621 አባላት ረቂቁን ሕገ መንግሥት ሲደግፉ፡ 13 ተቃውመውታል፤ 11 ደግሞ ድምፅ ከመስጠት ታቅበዋል።

ሕገ መንግሥቱ ተግባራዊ እንዲሆን ሕዝበ ውሳኔ መደረግ ይኖርበታል። ሕዝበ ውሳኔው የሚደረግበት ጊዜ ግን ገና አልታወቀም።

የተመድ ዋና ፀሐፊ ፓን ኪ ሙን በሶማልያ መንግሥታዊ ተቋማትን ለመገንባት እንዲረዳ የተዘጋጀው እና በተመድ የሚደገፈው ዕቅድ አካል የሆነው ይኸው ሕገ መንግሥት መፅደቁን ታሪካዊ ሲሉ አሞግሰውታል። አዲሱ ሕገ መንግሥት ሶማልያን በማረጋጋቱ ላይ ዋና ሚና ሊጫወት እንደሚችልም ነው የሶማልያ የሽግግር መንግሥት ባለሥልጣናት፡ የአፍሪቃ ህብረትና የሚደግፉዋቸው መንግሥታት የገለጹት። ይሁንና፡ እንደ የደቡብ አፍሪቃው የዓለም አቀፉ የፀጥታ ጥናት ተቋም የፖለቲካ ተንታኝ ኤማኑዌል ኪሳንጋኒ ግምት፡ የሶማልያ ፖለቲከኞች ያስተሳሰብ ለውጥ እስካልሳዩ ድረስ ሕገ መንግሥት ማፅደቁ ብቻውን በሽግግሩ መንግሥት አንፃር አሁንም ምንም እንኳን ከአሚሶምና ከመንግሥት ጦር ኃይል ባረፈበት ግፊት ቢዳከምም፡ ውጊያውን ባላቆመው አሸባብ ስጋት የተደቀነባትን ሶማልያን ለማረጋጋት ያን ያህል ፋይዳ አይኖረውም።«ሰዎች ባሕሪያቸዉን ለዉጠዉ ለሕገ መንግሥቱ ለመገዛት እስካልፈቀዱ ድረስ ሕገ መንግሥት ማለት ያዉ ሰነድ ማለት ነዉ። ብቻዉን ሰላም ሊያሰፍን አይችልም። ይሁንና አግባቢ ተቀባይነት ካለዉ ፖለቲከኞች ያንን ገቢራዊ ማድረግ አለባቸዉ።»

ባጠቃላይ የተለያዩ የሶማልያ ህብረተሰብ አባላት፡ ምንም እንኳን ሕገ መንግሥቱ መፅደቁን አዎንታዊ ሆኖ ቢያዩትም፡ በረቂቁ ላይ የተደረገው ክርክር ሂደት ላይ ቅሬታ አላቸው። ኪሳንጋኒ እንዳስረዱት፤
« ሸንጎው ሁሉን ያቀፈ አልነበረም በሚል ቅሬታ የሰነዘሩ አሉ። የሸንጎው አባላት በተሰየሙበት ድርጊት ላይ ጥቂቶች፡ በተለይም፡ ፖለቲከኞች ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳሳረፉና በረቂቁ ላይ የተካሄደው ክርክርም የተጣደፈ ነበር በሚል ወቅሰዋል። በሌላ በኩል ሌሎች የሶማልያ የሽግግር መንግሥት የሥልጣን ጊዜ የፊታችን ነሀሴ ሀያ 2012 ዓም በሚያበቃበት ጊዜ በሀገሪቱ የሥልጣን ክፍተት እንዳይፈጠር የሚያስቻል ነው በሚል ሕገ መንግሥቱ ቶሎ መፅደቁን ደግፈውታል። »ይኸው የተለያዩ የሶማልያ ህብረተሰብ አባላት ቅሬታ የሰላሙን ሂደት ሊጎዳ ይችላል ሲሉ የተመድ ልዩ የሶማልያ ተጠሪ አውጉስቲን ማሂጋ አስጠንቅቀዋል።
ጥንቃቄ በሚጠይቀው የሶማልያ የሰላም ሂደት ላይ በሸንጎው የተጠቃለሉት የጎሣ ሽማግሌዎች አዲስ ምክር ቤት የሚሰይሙበትና ይኸው ምክር ቤትም ነሀሴ ሀያ የሀገሪቱን ፕሬዚደንቱን የሚመርጥበት ሂደት ዋነኞቹ ርምጃዎች ይሆናሉ። አዲሱ ሕገ መንግሥት ያለፉት ሀያ አንድ ዓመታት ቀውስ ያልተላቀቃትን ሶማልያ ለማረጋጋት የሚበጅ መሆኑን የአፍሪቃ ህብረት ልዩ ልዑክ ቡባካር ዲያራ ቢያስታውቁም፡ ምክር ቤቱ እና ፕሬዚደንቱ ምርጫ በትክክለኛ እና በታማኝ ዘዴ ሊካሄድ እንደሚገባው አሳስበዋል። ሸንጎው በሕገ መንግሥቱ ላይ ድምፅ ሊሰጥ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ሸንጎው ተሰብስቦበት በነበረው ቦታ አካባቢ አጥፍቶ ጠፊዎች ሊጥሉት የነበረ ጥቃት መክሸፉ ሲታወቅ፡ አንድ በሽግግሩ መንግሥት ላይ የሚቀልድ ኮሜድያን በትናንቱ ዕለት ተገድሎዋል።

አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic