የሶማሊያ ሁኔታ | ኢትዮጵያ | DW | 23.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሶማሊያ ሁኔታ

የኬንያ መንግሥት አክራሪ ሐይላት ሶማሊያን ሲቆጣጠሩ «እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም» ባይ ነዉ።ኢትዮጵያ ግን አለም አቀፍ ማሕመረሰብ ሐላፊነት እስካልሰጣት ድረስ ከዚሕ ቀደም እንዳደረገችዉ ጣልቃ እንደማትገባ አስታዉቃለች

default


ከኢትዮጵያ ሶማሌ-ክልል ወደ ሶማሊያ ሥንሻገር ግጭት ዉጊያዉ ዛሬም እንደመሰንበቻዉ የመቆም ምልክት አልታየበትም።የሐገሪቱ ደካማ የሽግግር መንግሥት ፕሬዝዳት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አሕመድ ትናንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግገዋል።የሽግግር ምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ደግሞ መንግሥታቸዉን ከእስላማዊ ጠላቶቹ ጥቃት ለማዳን ጎረቤት ሐገራት ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል።የኬንያ መንግሥት አክራሪ ሐይላት ሶማሊያን ሲቆጣጠሩ «እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም» ባይ ነዉ።ኢትዮጵያ ግን አለም አቀፍ ማሕመረሰብ ሐላፊነት እስካልሰጣት ድረስ ከዚሕ ቀደም እንዳደረገችዉ ጣልቃ እንደማትገባ አስታዉቃለች።የግጭቶችን ምክንያትና መፍትሔ የሚያጠናዉ ክራይስሰ ግሩፕ የተሰኘዉ ተቋም የሶማሊያ ጉዳይ አዋዊ ረሺድ አብዲ እንደሚሉት ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ሆነ የዉጪዉ ጣልቃገብነት የሶማሊያን ግጭት ለማስወገድ ብዙም አይፈይዱም።ረሺድ አብዲን ሉድገር ሻዶምስኪ አነጋግሯቸዋል።አጭር ትርጉሙን እነሆ።

-------------

ከአምስት አመት በፊት የሶማሊያ የሸግግር መንግሥት እንዲመሠረት ከፍተኛ ጥረት ካደረጉት አንዱ የነበሩት ኬንያዊዉ ዲፕሎማት ኪፕ ላጋርት በበኩላቸዉ የአለም አቀፉ ማሕበረሰብ ድጋፍ እስካልተገኘ ድረስ ጎረቤት ሐገሮች ሶማሊያ ዉስጥ ጣልቃ መግባት የለባቸዉም ይላሉ።

ነጋሽ መሐመድ/ሂሩት መለሰ