የሶማሊያው ጦርነትና በምስራቅ አፍሪቃ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር | ኢትዮጵያ | DW | 09.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሶማሊያው ጦርነትና በምስራቅ አፍሪቃ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር

በህግ አልባዋ ሶማሊያ የሰፈነው ስርዓተ አልበኝነት ምስራቅ አፍሪቃ ዋነኛ የወንጀል ማዕከል እንድትሆን እገዛ እያደረገ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ ።

default

የድርጅቱ የአደንዛዥ ዕፅና የወንጀል ጉዳዮች ተከታታይ ቢሮ ሀላፊ አንቶንዮ ማርያ ኮስታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እንዳስታወቁት በአካባቢው የተስፋፋው የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሌሎች ህገ ወጥ ዕንቅስቃሴዎች ለችግሩ መጠናከር አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው ። በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታዎች አስተባባሪ ቢሮ በበኩሉ በሶማሊያ የተደራጀ ወንጀል መስፋፋት የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን ስጋት ውስጥ እንደጣለው አስታውቋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ