የሶማሊያዉ ፕሬዝዳት በዩናይትድ ስቴትስ | ኢትዮጵያ | DW | 07.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሶማሊያዉ ፕሬዝዳት በዩናይትድ ስቴትስ

የፕሬዝዳቱን ጉብኝትና በየስፍራዉ ያደረጉትን ዉይይት ያደራጁት እንደሚሉት ሸኽ ሸሪፍ አሜሪካ በሚኖሩት ሶማሊያዉያን ዘንድ ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት እያገኙ ነዉ

default

የሶማሊያዉ ፕሬዝዳት ሼኽ ሸሪፍ ሸኽ አሕመድ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ከሚኖሩ ሶማሊያዉያዉያን እና ሶማሊያዉያን አሜሪካዉያን ጋር የሚያደርጉትን ዉይይት እንደቀጠሉ ነዉ።በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ከሁለት ሳምንት በፊት ኒዮርክ የገቡት ፕሬዝዳት ሸርፍ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች እየተዘዋወሩ በየአካባቢዉ ለሚኖሩ የሶማሌ ተወላጆችና ወዳጆች ገለፃና ማብራሪያ አድርገዋል።የፕሬዝዳቱን ጉብኝትና በየስፍራዉ ያደረጉትን ዉይይት ያደራጁት እንደሚሉት ሸኽ ሸሪፍ አሜሪካ በሚኖሩት ሶማሊያዉያን ዘንድ ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት እያገኙ ነዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።

አበበ ፈለቀ/ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic