የስፖርት ጥንቅር-ጥቅምት 15፤ 2008 ዓ,ም | ስፖርት | DW | 26.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የስፖርት ጥንቅር-ጥቅምት 15፤ 2008 ዓ,ም

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ እሁድ ጥቅምት 15 2015 ዓ,ም በተካሂደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባለድል ሆነዋል።


በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ እሁድ ጥቅምት 15፣ 2015 ዓ,ም በተካሂደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባለድል ሆነዋል። አንጎላን እና ጋቦንን ተከትለው ዋልያዎቹ ሩዋንዳ ለምታካሂደው የቻን አፍሪካ ዋንጫ፡ አላፊ መሆናቸውን ትላንት አረጋገጡ ። የ 62 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ባለሀብት እና የቀድሞ የፖለቲካ እስረኛ ቶኪዮ ሳክ ዋሌ የዓለም እግር ኳስ ማህበርን ለማስተዳድር በእጩነት እንደቀረቡ አስተወቁ። የአውሮጳ እግር ኳስ ማህበር በአራት አውሮጳ ሀገራት ላይ በያዝነው ወር ለአውሮፓ ሻንፒዮን ማጣሪያ ባደረጉት ጨዋታ ደጋፌዋቻቸው በሳዩት ያልተገባ ባህሪ የገንዘብ ቅጣት መጣሉን አርብ ዕለት አስታውቅዋል።
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የርገን ክሎፕ ለሶስትኛ ግዜ አቻ ወጡ። በጀርመን ቡንዲስ ሊጋ ባየርሙንሽን ለአስረኛ፡ ግዜ የሊጋውን ጨዋታ አሽነፈ። ትላንት የአሜሪካ በተካሂደው የግራንድ ፕሬክስ የፎርሙላ ዋን የመኪና ውድድር ሉዊስ ሀሚልተንን አሽናፊ ሆነ። ሀሚልተንን የዘንድሮን የፎርሙላ ዋን ውድድር ለሶስትኛ ጊዜ ማሸነፍ የሚሉት አና ሌሎችም ተካተዋል ።
ሃና ደምሴ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic