የስፖርት ጥንቅር _ ጥቅምት አንድ፣ 2008 ዓም | ስፖርት | DW | 12.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የስፖርት ጥንቅር _ ጥቅምት አንድ፣ 2008 ዓም

በሩስያ እአአ በ2018 ዓም ለሚደረገው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ በሳምንቱ መጨረሻ አፍሪቃን ወክለው ለማለፍ በተለያዩ የሀጉሪቱ ከተማዎች የመለያ ውድድሮች ተካሄደዋል። እሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ፤ ታንዛኒያ ፤ኬንያ እና ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ውድድር ኃላፊ ሆነዋል። ቀጣዩ የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ኮንጎ ብራዛቪል ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:10
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:10 ደቂቃ

ስፖርት

በቻይና በተካሄደው የወንዶች የሜዳ ቴኒስ ውድድር ሰርቢያዊው ኖቫክ ዶኮቪች፣ በሴቶች ደግሞ ስጳኛዊቱ ጋርቢን ሙጉሩዛ አሸናፊዎች ሆነዋል። በሶቺ፣ ሩስያ መኪና እሽቅድድም ብሪታንያዊው ልዊስ ሀሚልተን በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 302 ከፍ አድርጓል። ጀርመን፣ ፖላንድ ፣ አልባንያ እና ሩሜንያ ፈረንሳይ እአአ በ2016 ዓም ለምታስተናግደው የአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያ አልፈዋል።

ሃና ደምሴ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic