የስደት እንግልትና መፍትሄው | ኢትዮጵያ | DW | 07.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የስደት እንግልትና መፍትሄው

በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ተነስተው የሜድትራንያንን ባህር አቋርጠው ወደ አዉሮፓ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ከአዉሮጳ ሌላ ደቡብ አፍሪቃም ብዙዎች የሚሰደዱባት ሃገር ናት። ስደት ቀላል አይደለምና መንገድ ላይም ሆነ በሄዱበት የሚንከራተቱ ፣ከዚያም በላይ ሕይወታቸዉን የሚያጡም ጥቂቶች አይደሉም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:36

የስደት እንግልትና መፍትሄው

ሰሞኑም በሕገወጥ መንገድ ማላዊ ገብተዋል የተባሉ 120 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ ሕፃናት ጭምር እንደታሰሩ ተዘግቧል ። « ሴንተር ፎር ሂውመን ራይትስ ሊጋል ሪሶርስ» የተሰኘዉ የሰብዓዊ መብት ተካራካሪ ቡድን ጉዳያቸዉን እንደሚከታተል ገልጾ የተወሰኑ ስደተኞች ካለፈው ሁለት ዓመታት አንስቶ እስር ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።


የማላዊ የፍልሰት መሥሪያ ቤት የተያዙት ህጋዊ ሰነድ እንዴሌላቸዉ እና የደህንነት ችግር ይፈጥራሉ ተብሎ በመሰጋቱ እንደታሰሩና ስደተኞቹን ለመመለስም ገንዘብ እንዴሌለዉ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ያለው የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት «አይ ኦ ኤም»ም ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን እና ስደተኞቹን ወደ ሃገራቸው ለመመለስም ተቋሙ ከመንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰራ የመሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የኮሙኒኬሼን ረዳት አቶ አለማየሁ ሰይፈሥላሴ ለደዶቼ ቬሌ በኢሜል አስረድተዋል።


ወጣቱ እንዲሰደድ አንዱ እና ዋና ምክንያት የሆነዉ ስራ አጥነት ሲሆን መንግስት ስራ እንድፈጥሩ አላበረታታም፣ በስደተኞች መታሰር እና መሞት ፣ መንግስት ተጠያቂ ነው ሲሉ በሃዲያ/ኦሳና ነዋሪ የሆኑት መምህር ወንድማገኝ አለማዬሁ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።


አብዛኛዉ ወጣት ለተሻለ ህይወት ፍለጋ ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍርቃ የሚሰደደው ከሃድያ መሆኑን መምህር ወንድማገኝ ገልፀው እሳቸዉም ደሞዛቸውም ለቤት ኪራይ እንኳን የማይበቃ በመሆኑ የመሰደደ እቅድ እንዳላቸዉ ተናግረዋል። (ሳዉዲ አረብያ ጅዳ አከባቢ ነዋሪ የሆነዉ ተመስገን ሃይሉ ኢትዮጵያን ለቆ ለመሰደድ የበቃው ሥራ በማጣቱ ነው ። በበኩሉ መንግስት ስደትን ማስቆም ያልቻለበት ምክንያት የሚለውን ተናግሯል።


በማላዊም ሆነ በሌሎች ቦታዎች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ ባይታወቅም የሚሰደዱት «አገርቤት በቁመ ከምሞት እዉነተኛዉን ሞት መሞት ይሻላል»> በሚል ምክንያት ነው ይላሉ አቶ ተመስገን ። ስለ ጉዳዩ በዶይቼ ቬሌ የፈስቡክ ድረ ገፅ ከተሰጡት አስተያየቶች አንዱ «ሰው ክቡር ነው ወዶና ፈቅዶ ወደሞት አይሄድም ቢቸግረው ግራ፣ ቢገባው ነው እና የኢትዮጵያ መንግስት ቢያንስ ምግብ ወደ ውጭ ባይልክ ምግብ ያለቀረጥ ቢገባ መልካም ይመስለኛል በኔ ግምት፣» የሚል ነው ። ሌሎቹ ደግሞ « መንግስት ፣ለህዝብ የሚጠቅም ስራ መሰራት አለበት፣ ከልሆነ የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ አይሄድም» ሲሉ አስተያየታቸዉን አስፍረዋል።

መርጋ ዮናስ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic