የስደተኞች ጫና ከጣሊያን ወደ ባልካን | ዓለም | DW | 08.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የስደተኞች ጫና ከጣሊያን ወደ ባልካን

ሰሞኑን ወደ ጣሊያን የሚገባዉ የስደተኛ ቁጥር በተነፃፃሪነት ሲቀንስ በምሥራቅ አውሮጳ የባልካን ሃገራት የስደተኞቹ ፍልሰት እየጨመረ ነው። በሺህዎች የሚቆጠሩ በተለይ የሶሪያ ስደተኞች በመቄዶኒያ እና ሐንጋሪ አድርገው ወደ ኦስትሪያ እና ጀርመን ተመዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:31

የስደተኞች ጫና ከጣሊያን ወደ ባልካን

ጀርመን 800 ሺህ ስደተኞችን ተቀብላ ከህብረተሰቡ ጋር ተዋህደው እንዲኖሩ ማድረጉ ይሳካልኛል ብላ እንደምታስብ ገልጣለች። የቀኝ አክራሪ ብሔርተኛ መንግሥት በሚመራት ሐንጋሪ ደግሞ በመዲናይቱ ቡዳፔስት ዋናው ባቡር ጣቢያ እና በተለያዩ ቦታዎች ስደተኞቹ እንግልት ሲደርስባቸውም ተስተውሏል። የጣሊያን መንግሥት በርካታ ስደተኞች መኖሪያ ቀዬያቸውን ጥለው የሚወጡባቸው ሃገራት ተለይተው ኹኔታቸው ሊጠና ይገባል ብሏል። ሕገ-ወጥ የስደተኞች አዘዋዋሪዎች ላይም ጠንከር ያለ ርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አስተላልፈዋል። የሮሙ ወኪላችን ተክለእዝጊ ገብረ እየሱስ ዘገባ አለው።

ተክለእዝጊ ገብረ እየሱስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic