የስደተኞች ጥያቄ እና የአውሮጳ ጭንቀት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የስደተኞች ጥያቄ እና የአውሮጳ ጭንቀት

እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከሆነ በዓለም ዙሪያ 60 ሚሊዮን ስደተኞች ይገኛሉ። ወደ አውሮጳ ከተሰደዱት መካከል ጀርመን በርካታቶችን ወደ ሀገሯ በማስገባት ቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛለች።

ይሁንና በስደተኞች ጥያቄ ውዝግብ ላይ ያለችው ሀገር ፖለቲከኞች በአሁኑ ሰዓት ድንበር ይዘጋ አይዘጋ ክርክር ላይ ናቸው። ይሄው የስደተኞች ጉዳይ ዳቮስ -ሲውዘርላንድ ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ዋና የመወያያ ርዕስ ነው። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዩሀይም ጋውክ ዛሬ በተለይ የምስራቅ አውሮጳ ሀገሮች የስደተኞችን የተገን ጥያቄ በተመለከተ ትብብር እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። አሳሳቢው የስደተኞች ጉዳይን አስመልክቶ፤ በጀርመን እና በአጠቃላይ በአውሮጳ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ወኪሎቻችንን፤ ከበርሊን ይልማ ኃይለሚካኤልን እና ከብራስልስ ገበያው ንጉሴን አነጋግረናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል/ ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic