የስደተኞች ጎርፍ በፈረንሣይ | አፍሪቃ | DW | 04.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የስደተኞች ጎርፍ በፈረንሣይ

ከአፍሪቃ እና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወደ አውሮጳ የሚጎርፉ ስደተኞች በፈረንይዋ የወደብ ከተማ ካላይ አሳብረው በቅርብ ርቀት ወደ ምትገኘው እንግሊዝ ለመግባት በመጉረፍ ላይ ናቸው።

ስደተኞች በሰሜን ፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካላይ ከተማ ከምንጊዜውም በላይ በመጉረፍ ላይ ናቸው። ምክንያቱ ደግሞ ከእዚህች የወደብ ከተማ ወደ ታላቋ ብሪታንያ ለመግባት ርቀቱ ከ30 ኪሎ ሜትሮች ያለመብለጡ መሆኑ ተገልጿል። ልክ በድርጊት የተሞሉ ፊልሞች ላይ እንደሚሆነው ሁሉ ስደተኞች በሰፋፊ አውራ መንገዶች ላይ በፍጥነት በሚሽከረከሩ የጭነት መኪናዎች ላይ እየተሯሯጡ በአደገኛ ሁናቴ ሲጫኑ መመልከት የተለመደ ሆኗል። በአጠቃላይ በፈረንሣይዋ የካላይ ከተማ ስደተኞችን በተመለከተ ሁኔታዎች ከቀን ቀን እየተወሳሰቡ መምጣታቸው እየተነገረ ነው። ጊዮርግ ማቲያ ስ ስደተኞቹ ን በቦታው ተመልክቶ የላከውን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው አቀናብሮታል።

ጊዮርግ ማቴስ/ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic