የስደተኞች ጉዳይ፣ የአውሮጳ ህብረት አስቸኳይ ጉባዔ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 07.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የስደተኞች ጉዳይ፣ የአውሮጳ ህብረት አስቸኳይ ጉባዔ

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች አውሮጳን ከብዙ ጊዜ አንስቶ እያወዛገበ ላለው የስደተኞች ጥያቄ መፍትሔ ለመሻት ዛሬ አስቸኳይ ጉባዔ ጠርተዋል።

በአህጉሩ የሚገኙትን ስደተኞች አባል ሀገራት በመካከላቸው በፍላጎት ለመከፋፈል ካሁን ቀደም የደረሱት ሰምምነት እስካሁን ከሞላ ጎደል ተግባራዊ ላልሆነበት ድርጊት እና ትልቅ ልዩነት ለፈጠረው ለዚሁ ሁኔታ መልስ ለማፈላለግ ይሻሉ። ከዚህ በተጨማሪ፣ በዚሁ ጉባዔ ላይ ህብረቱ ወደ አህጉሩ በህገ ወጥ መንገድ የሚገቡትን ስደተኞች ቁጥር ለመቀነስ እና በአህጉሩ መቆየት የማይቀድላቸውንም ወደቱርክ ለመመለስ በሚያደርገው ጥረቱ ላይ ትብብሯን የሚፈልገውን በወቅቱ የሰብዓዊ መብት ትረግጣለች የምትባለዋን ቱርክ ጋብዞዋል። ስለአውሮጳ ህብረት አስቸኳይ ጉባዔ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት የብራስልስ ወኪላችንን ገበያው ንጉሤን አነጋግሬው ነበር።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic