የስደተኞች ከፍተኛ ችግር በበሊቢያ | አፍሪቃ | DW | 04.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የስደተኞች ከፍተኛ ችግር በበሊቢያ

ሳባ ተብሎ የሚጠራዉ ሊቢያ ዉስጥ የሚገኝ የስደተኞች እና የተገን ጠያቂዎች ማቆያ ማዕከል ቁጥራቸዉ ከ 300 በላይ የሚደርሱ ስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች በጣም በተጣበበ ቦታ እንደሚኖሩና እጅግ አስደንጋጭ በሆነ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።


ሳባ ተብሎ የሚጠራዉ ሊቢያ ዉስጥ በሚገኝ የስደተኞች እና የተገን ጠያቂዎች ማቆያ ማዕከል ቁጥራቸዉ ከ 300 በላይ የሚደርሱ ስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች በጣም በተጣበበ ቦታ እንደሚኖሩና እጅግ አስደንጋጭ በሆነ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ። ስደተኞቹ በከፍተኛ ጤና ችግር ላይ ይገኛሉ፤ ጉዳዩ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነዉ ያለዉ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን «MSF» በማቆያ ጣብያዎች በከፍተኛ የሰብዓዊ ችግር ዉስጥ በተለይ እድሜያቸዉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናት በማዕከሉ ውስጥ እንዲኖሩ መገደዳቸው  እንዲቀር ሲል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪዉን አቅርቦአል።  የዓለምአቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን  «UNHCR» በሊቢያ ያለዉ የስደተኞች አልያም የተገን ጠያቂዎች መጠለያ እንዲዘጋ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርግ  እንደነበር ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን አስታዉቋል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ


አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሠ