የስደተኞች እልቂት | ዓለም | DW | 01.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የስደተኞች እልቂት

ስደተኞቹን ለማዳንና ለመርዳት የአዉሮጳ ሕብረት እንዲተባበረዉ ላቀረበዉ ጥያቄ ሕብረቱ ተገቢ መልስ አልሰጠም በማለት ወቅሶታል።በተያያዘ ዜና የኢጣሊያ ፀጥታ አስከባሪዎች 16 ስደተኛ አሸጋጋሪዎች መያዛቸዉን አስታዉቀዋል።አንዱ ኢትዮጵያዊ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:36
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:36 ደቂቃ

የስደተኞች እልቂት

ባለፈዉ ሳምንት የሜድትራኒያን ባሕርን አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1000 መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) እንደሚለዉ የጎሮጎሪያኑ 2016 ከባተ ጀምሮ ባንድ ሳምንት በርካታ ስደተኞች ሲያልቁ ያለፈዉ ሳምንቱ ከፍተኛዉ ነዉ።የኢጣሊያ መንግሥት በበኩሉ ስደተኞቹን ለማዳንና ለመርዳት የአዉሮጳ ሕብረት እንዲተባበረዉ ላቀረበዉ ጥያቄ ሕብረቱ ተገቢ መልስ አልሰጠም በማለት ወቅሶታል።በተያያዘ ዜና የኢጣሊያ ፀጥታ አስከባሪዎች 16 ስደተኛ አሸጋጋሪዎች መያዛቸዉን አስታዉቀዋል።አንዱ ኢትዮጵያዊ ነዉ።ሥለ ስደተኞች እልቂት፤ ብዛትና የአሸጋጋሪዎቹ ማንነት የሮም ወኪላችንን ተኽለእግዚ ገብረእየሱስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ተኽለእግዚ ገብረእየሱስን

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic