የስደተኞች ታሪክን የሚያወሳዉ ቤተ-መዘክር | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የስደተኞች ታሪክን የሚያወሳዉ ቤተ-መዘክር

ባለፈዉ ሳምንት ፓሪስ ፈረንሳይ ዉስጥ የስደተኞችን ታሪክ የሚያሳይ ቤተ መዘክር ተመረቀ።

የቤተ መዘክሩ ሃሳብ በቀድሞዉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ ተጠንስሶ እንደ ጎርጎረሳዊዉ አቆጣጠር በ2007 ዓ,ም ግንባታዉ ቢጠናቀቅም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩት ኒኮላ ሳርኮዚ ቤተመዘክሩን ለመመረቅም ሆነ ለመጎብኘት ፍላጎት ባለማሳደራቸዉ ምክንያት ይፋዊ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ሳይደረግለት ላለፉት ሰባት ዓመታት ለመዘግየት ተገዷል። ቤተ መዘክሩን መርቀዉ የከፈቱት ፕሬዚደንት ፍራንሶዋ ኦላንድ፤ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ስደተኞችን በተመለከተ ሰፊ ግዜ ሰጠዉ ባደረጉት ንግግር የዛሬይቱ ፈረንሳይ በመጤዎች መልካም ተግባር መገንባትዋን አፅኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል። ፀረ-ስደተኛ ስሜት ያላቸዉን ፖለቲከኞችም አዉግዘዋል።

ሐይማኖት ጥሩነህ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic