የስደተኞች ቀን በአዲስ አበባ | ዓለም | DW | 18.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የስደተኞች ቀን በአዲስ አበባ

ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህፃሩ IOM ጄኔቫ ላይ ዛሬ እንዳስታወቀዉ በመገባደድ ላይ ባለዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ብቻ ወደአዉሮጳ የገቡ ስደተኞች ቁጥር በቀጣይ ቀናት አንድ ሚሊየን እንደሚደርስ አመልክቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:57

የዓለም አቀፍ ስደተኞች ቀን

IOM ስደተኞችን ያሰበበትን ዓለም አቀፍ ቀን በአዲስ አበባ እያከበረ ነዉ። በመላዉ ዓለምም ተገደዉ ለስደት የተዳረጉ ወገኖች ቁጥር በሚሊየኖች እንደሚቆጠርም IOM አስታዉቋል። በአዲስ አበባ ከተማ በኦሮሞ የባህል ማዕከል ስደተኞችን የዘከረዉ የድርጅቱ ልዩ አስተባባሪ የተሰደዱ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ይህን ያህል ነዉ ለማለት እንደሚያዳግት ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic