የስደተኞች መስመጥ | ኢትዮጵያ | DW | 16.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የስደተኞች መስመጥ

ሰሞኑን አብዛኛ ሕዝቧ ሐዘን ተቀምጧል። ምክንያት? ወደ አረብ ሐገር ለመሰደድ ከቤታቸዉ ከወጡ የወረዳዉ ወጣቶች በትንሽ ግምት 40ዉ አደን ባሕረ-ሰላጤ ሰጥመዉ ሞቱ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:18

የአንድ ወረዳ ልጆች አንድ ላይ ሞቱ

አፅቢ-ወንበራ ምስራቅ ትግራይ የምትገኝ ወረዳ ናት። ሰሞኑን አብዛኛ ሕዝቧ ሐዘን ተቀምጧል። ምክንያት? ወደ አረብ ሐገር ለመሰደድ ከቤታቸዉ ከወጡ የወረዳዉ ወጣቶች በትንሽ ግምት 40ዉ አደን ባሕረ-ሰላጤ ሰጥመዉ ሞቱ። ባለፈዉ መጋቢት 28 አነስተኛ ጀልባ ተሳፍረዉ ከጅቡቲ ወደ የመን በመቅዘፍ ላይ እንዳሉ ሰጥመዉ  የሞቱት ሰዎች ቁጥር 70 ይደርሳል ነዉ የተባለዉ። ከሟቾቹ ቢያንስ አርባዉ የአንድ ወረዳ ወጣቶች ናቸዉ። የአፅቢ ወንበራ። ኢትዮጵያዊ ወጣት አደጋ እንደሚገጥመዉ እያወቀ  በብዛት የመሰደዱ ሰበብ ምክንያት ዛሬም እያነጋገረ ነዉ።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች