የስደተኞችን ፍሰት ለመግታት ያለመዉ ጉባኤ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የስደተኞችን ፍሰት ለመግታት ያለመዉ ጉባኤ

 በዛሬዉ ዕለት በተለያዩ ሁለት የአዉሮጳ ከተሞች አዉሮጳን በተለይም የአዉሮጳ መዳረሻ ወደሆነችዉ ጣሊያን የሚጎርፈዉን የስደተኛ ብዛት መግታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመምከር ስብሰባዎች እየተካሄዱ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:37

ለጣሊያን አቤቱታ የአዉሮጳ ምላሽ፤

የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢስቶኒያ ዋና ከተማ ታሊን ተሰባስበዉ በስደተኞች ብዛት የተጨነቀችዉ ጣሊያንን መርዳት በሚችሉበት መንገድ ላይ መክረዋል። ሮም ላይ ደግሞ የአዉሮጳ ኅብረት እና የአፍሪቃ ዲፕሎማቶች የተመድ እና የዓለም የስደተኞች ድርጅት ባለስልጣናት በተገኙበት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሚታየዉን ቀዉስ የተመለከተ ዉይይት እያካሄዱ ነዉ። የአዉሮጳ ኅብረት የስደተኞች መብዛት ያስጨነቃት ጣሊያንን ለመርዳት ያቀርባል የተባለዉ አዲስ እቅድ ምን ምን ያካትታል በሚል ወደ ብራስልስ ደዉዬ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን ጠይቄዉ ነበር።

በሌላ በኩል ካለፈዉ ጥር ወር ወዲህ ከ80 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ግዛቱ እንደገቡ የተገለጸዉ ጣሊያን የአዉሮጳ ኅብረት አባል አጋሮቿ አንድ መፍትሄ እንዲፈልጉ ከሰሙን ጥሪ አቅርባለች። ጣሊያን ባቀረበችዉ ጥያቄ መሠረት የጣሊያን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሳምንቱ መጀመሪያ አስቀድመዉ የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ የሚፈልሱ ሰዎችን በተመለከተ የተቀናጀ እና ተጨባጭ ምላሽ ለመስጠት መክረዋል። መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም መፍትሄ የሚሉትን ሃሳብ እያቀረቡ ነዉ።  የሮሙ ዘጋቢያችን  ተከታዩን ልኮልናል

ገበያዉ ንጉሤ/ተኽለእዝጊ ገብረ ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic