የስደተኞችን ቀዉስ ለመግታት የአዉሮጳ ሕብረት ያደረገዉ ስብሰባ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የስደተኞችን ቀዉስ ለመግታት የአዉሮጳ ሕብረት ያደረገዉ ስብሰባ

የስደተኞች መግብያና መናሃርያ የሆኑ የአዉሮጳ ሕብረትና የባልካን ሃገራት መሪዎች እየጨመረ በመጣዉ የስደተኞች ቀዉስ ላይ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ብራስልስ የጋራ ስብሰባ አካሂደዋል።

ብረስልስ ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ በስደተኞች ጉዳይ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ጉባዔዎች ያላቋረጡ ሲሆን የአሁኑ ስብሰባ ደግሞ የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዣን ክሎድ ዩንከር ከጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና ከሌሎች መሪዎች ጋር በመመካከር የጠሩት መሆኑ ታዉቋል። በጉባዔዉ በስደተኞች ቀዉስ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት አስራአንድ የአዉሮጳ ሃገራት እና የባልካን ሃገራት ማለት የሰርብያ አልባንያና መቂዶንያ መሪዎች መካፈላቸዉ ታዉቋል።


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic