የስዑዲ የአካቢቢ ምርጫና የኢትዮጵያ የኮንትራት ሰራተኞች | ዓለም | DW | 17.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የስዑዲ የአካቢቢ ምርጫና የኢትዮጵያ የኮንትራት ሰራተኞች

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ ንጉሳዊው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የወሰደው ታሪካዊ እርምጃ ሲሉ አወድሰውታል። ተሳትፎውን የይስሙላ ያሉትም አልጠፉም። በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ የሳዉዲ አረብያ አሹራ ምክር ቤት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎች አገራትም የቤት ሠራተኞች ለኮንትራት ሥራ እንዲገቡ መፍቀድ አለመፍቀድ ላይ ተነጋግሮ ነበር ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:58
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:58 ደቂቃ

የሳዉዲ ዓረብያ የአካቢቢ ምርጫባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ አካባቢያዊ ምርጫ በመምረጥና በመመረጥ ተሳትፈዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የእንስቶቹን የምርጫ ተሳትፎ ንጉሳዊው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የወሰደው ታሪካዊ እርምጃ ሲሉ አወድሰውታል። ተሳትፎውን የይስሙላ ያሉትም አልጠፉም። በዚሁ አካባቢያዊ ምርጫ 978 እንስቶች ከ5,938 ወንዶች ጋር በእጩነት መቅረባቸዉ ነዉ የተገለፀዉ። 130,000 እንስቶች በመራጭነት በተመዘገቡበት በዚሁ ምርጫ የወንድ ድምጽ ሰጪዎች ቁጥር 1.35 ሚሊዮን መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል። በሌላ በኩል በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ የሳዉዲ አረብያ አሹራ ምክር ቤት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎች አገራትም የቤት ሠራተኞች ለኮንትራት ሥራ እንዲገቡ መፍቀድ አለመፍቀድ ላይ ተነጋግሮ ነበር ። ስለዚህና በሳምንቱ መጨረሻ ለመጀመርያ ጊዜ ሴቶች ስለተሳተፉበት የአካባቢያዊ ምርጫ አዜብ ታደሰ የሳዉዲ በሳዉዲ አረብያ የሚኖረዉን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን አነጋግራዋለች ።

ነብዩ ሲራክ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic