1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስኳር ኮርፖረሸን ቅሌት

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ ግንቦት 10 2008

የኢትዮጵያ የስኳር ኮርፖሬሸን 10 የስኳር ፋብርካዎችን ለመገንባት ያቀደዉ ከስድስት ዓመታት በፊት ነበር። ቆየት ብሎ በተከለሰዉ እቅድ መሠረትም የፋብሪካዎቹ ቁጥር ተቀንሶ ሰባት እንዲሆን ተደርጎም ነበር። የተጠቀሰዉን ፕሮጀክት ለማከናወን ደግሞ ከዉጭ እና ከሀገር ዉስጥ በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር ከዉጭ መበደሩም ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/1Iq2j
Karte Äthiopien englisch

[No title]

ይሁን እንጅ ከኮርፖሬሸኑ ባለስልጣናት አንዱ ግንቦት 1 2008 ዓ/ም በአገሪቱ ምክር ቤት በመንግሥት ኤንቴርፕራይዝ ቋሚ ኮሚቴ ፊለፊት ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ዘገባ በፕሮጀክቱ ከተያዙት የአንዱም የስኳር ፋብርካ ግንባታ እንዳልተጠናቀቀ ተናግረዋል።


በምክንያትነት ከተጠቀሱት መካከልም የስኳር ፋብርካዎቹን ግንባታ እንዲያጠናቅቅ ኃላፊፍነቱን የወሰደዉ የብረታ ብረት እና የኢንጅኔርንግ ኮርፖሬሸን እና የስኳር ኮርፖረሸን እንደታሰበዉ ሥራዉ ባለማከናወኑ ነዉ የሚለዉ ይገኝበታል። እንዲያም ሆኖ ከስኳር ኮርፖሬሽኑ ባለስልጣናት አንዱ መሥሪያ ቤታቸዉ ከተባለዉ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ጋር ምንም ዓይነት ዉል እንዳልፈጸም መናገራቸዉን ከሀገር ዉስጥ የሚወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ። ከዚህም ሌላ የተጠቀሰዉን ግንባታ ለማጠናቀቅ አቅሙ የለዉም ለተባለዉ የብረታ ብረት እና የኢንጅኔርንግ ኮርፖሬሽን ከ90 በመቶ በላይ ክፊያ እንደተደረገለትም መጥቀሳቸዉ ተገልጿል።


ከዉጭ እና ከሀገር ዉስጥ ገንዘብ ተበድሮ ለብዙ ዓመታት ሳይከፍሉ ቆይቶ መክፍያ ግዜ ሲቃረብ ፋብሪካዎቹ ሥራቸዉን አለመጀመራቸዉ ኮርፖሬሸኑን ከአቅም በላይ ወደሆነ ዕዳ ዉስጥ እንደከተተዉ የኤኮኖሚ እና የልማት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ዓለምአየሁ ገዳ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይህ ሊፈጠር የምችለዉም ይላሉ፣ የማቀድ አቅም ማንሳት፣ ሌሌላ የምንግስት ድርጅት ስራዉን ለመስራት ጠልቃ መግባቱ እና ህጋዊ ዉል አለመኖሩ ነዉ ስሉ ፕሮፌሶr አሌማዬሁ ጌዳ ያብራራሉ።

የኮርፖሬሸኑ ዕዳዉን መክፈል አለመቻል ኪሳራ እንደሚያስከትልበት የጠቀሱት ፕሮፌሶር አልማዬሁ አያይዘዉም የሀገሪቱ የገንዘብ ሁኔታ ላይም ተፅኖ እንዳለዉ አብራርቶዋል። የኢትዮጵያ የስኳር ኮርፖሬሸን ከዚህ ቀዉስ መዉጣት ከፈለገ እና ምክር የሚጠይቅ ከሆነ እንደ የኤኮኖሚ እና የልማት ባለሙያ የምመክሩት በደንብ ፕላን ማድረግ እና የስራ አፈፃፀሙ ላይ በደንብ መታሰብ እንዳለበት እንደሆነ ይናገራሉ።

በስኳር ኮርፖሬሸኑ በኩል በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ