የስኳርና የምግብ ዘይት ዕጥረት በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 06.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የስኳርና የምግብ ዘይት ዕጥረት በአዲስ አበባ

ኢትዮጵያ ወደ ዉጪ ከምትልከዉ ሸቀጥ የምታገኘዉ ገቢ ባለፉት ሥምንት ወራት በአርባ-ስምንት ከመቶ ማደጉን የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አስታዉቀዋል።

default

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ትናንት ለሐገሪቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች እንደነገሩት ከዉጪ ሺያጩ በተጨማሪ የእርሻ ምርትም በ12.57 በመቶ አድጓል።የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ግን በተለይ የስኳርና የምግብ ዘይት እጥረት እና የዋጋ ንረት አስቸገረን ይላሉ።የመንግሥት ባለሥልጣናት ለዚሕም «መፍትሔ ተበጅቶለታል»-ይላሉ።መፍትሔዉ የቅባት እሕል ወደ ዉጪ የምትልከዉ፥ ሽንኮራ እንደልብ የምታመርተዉ ሐገር ስኳርና የምግብ ዘይት ከዉጪ እያስገባች ነዉ ። አለማያሁ ተድላ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

አለማየሁ ተድላ

ነጋሽመሐመድ

ሂሩት መለሰ