የስኮትላንድ ውሳኔ ሕዝብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የስኮትላንድ ውሳኔ ሕዝብ

በሰሜናዊው ጫፍ የብሪታንያ ግዛት አካል ስኮትላንድ ፤ እጎአ በ2012 በተደረገ ስምምነት መሠረት፣ ተገንጥላ የራሷን ነጻነት ለማወጅ ወይም ከ 300 ዓመት በላይ ጸንቶ በቆየው ሕብረት፣ ዩናይትድ ኪንግደም በሚባለው ሀገር፣ ማለትም በብሪታንያ በሕብረት ለመኖር፤ ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ፣ ህዝቡ ከዛሬ ጧት አንስቶ እስከማታ ድምፁን በመስጠት ላይ ነው።

ከብሪታንያ ኑዋሪዎች ሌላ ፤ ሂደቱን በቤይጂንግ እስከ ዋይንግተን ፤ ከሞስኮ እስከ ኒው ደልሂ ፤ ሂደቱን ሃገራት በጥሞና በመከታተል ላይ ናቸው። ከአውሮጳም ውስጥ ፤ ድንገት ስኮትላንድ ብትገነጠል አርአያነቱ አሥጊ ሆኖ የታያቸው፤ እንደ እስፓኝ ፤ ፈረንሳይ ቤልጅግ፣ ኢጣልያ የመሳሰሉት ሃገራት ብቻ አይደሉም። ስለዛሬው የስኮትላንድ ውሳኔ ሕዝብ ፤ የለንደኗን ዘጋቢአችንን ሐና ደምሴን በስልክ አነጋግሬ ነበር።

ሐና ደምሴ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic