የስትራውስ ካን ክስና ድንገተኛዉ ለዉጥ | ዓለም | DW | 03.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የስትራውስ ካን ክስና ድንገተኛዉ ለዉጥ

የዓለምአቀፉ ምንዛሪ ተቋም የአይ.ኤም.ኤፍ. የቀድሞው አስተዳዳሪ ዶሚኒክ-ስትራውስ-ካን ላይ የተጣለዉ የወንጀል ክስ አጠራጣሪ ሁኔታን በመፍጠሩ የፈረንሳይን የፖለቲካ መድረክ አናግቶታል።

default

ካን የሚያራምዱት የፈረንሳዩ ሶሻሊስት ፓርቲ በመጭዉ 2012 የጎርጎረሳዉያኑ አመት በሚካሄደዉ ምርጫ ላይ ዶሚኒክ-ስትራውስ-ካን ፕሪዝደንት ሳርኮዚን በመቀናቀን ለፕሪዝደንትነት እንዲወዳደሩ ይፈልጋል። የ 62 አመቱ የቀድሞው የዓለምአቀፉ ምንዛሪ ተቋም የአይ.ኤም.ኤፍ. አስተዳዳሪ ከሰባት ሳምንት ቁም-እሥር በኋላ ነጻነታቸዉን በኒዮርክ በሚገኘዉ ቪላቸዉ እያጣጣሙ ይገኛሉ። የኒውዮርክ የፍርድ ባለሥልጣናት ከትናንት በስትያ ካንን ነጻ የለቀቁት አቃቤ-ሕጉ ክብሬን ደፍረዋል ስትል የከሰሰቻቸው የሆቴል ቤት የጽዳት ሠራተኛ የሰጠችውን ቃል የማይታመን አድርገው ካገኘው በኋላ ነው። ግለሰቧ በክሱ ዝርዝር ላይ መዋሸቷን እንዳመነችም ተጠቅሷል። የተከሳሹ ጠበቆች መላው ክስ ውድቅ እንዲሆን ጥሪ ቢያደርጉም ስትራውስ ካን ከሁለት ሣምንት በኋላ እስከሚካሄደው ችሎት ድረስ አሜሪካ ውስጥ መቆየት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል። የፈረንሣይ ሶሻሊስቶች ፓርቲ ዶሚኒክ-ስትራውስ-ካንን በአገሪቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በዕጩነት ለማቅረብ ታላቅ ተስፋን ነዉ የሰነቀዉ። ስትራውስ ካን በክሱ የተነሣ የምንዛሪ ተቋም አመራር ሥልጣናቸውን መልቀቃቸው አይዘነጋም።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን

ተዛማጅ ዘገባዎች