የስብርባሪ ብረታ-ብረት መጣያ የመሰለው ኅዋና፣ ወደፊት ሊያጋጥም የሚችለው አደጋ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 25.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የስብርባሪ ብረታ-ብረት መጣያ የመሰለው ኅዋና፣ ወደፊት ሊያጋጥም የሚችለው አደጋ፣

ለዘመኑ የሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ የምርምር ተቋማት፣ የጠፈር መንኮራኩር ማምጠቅ፣ ቀላል ነው። ችግሩ በሚላክ መንኮራኩር ሳቢያ ያልታሰበ ጣጣ እንዳያጋጥም፣ ከመከላከሉ ላይ ነው።

default

ከከባቢ አየር በላይ፣ ወደፊት ለምድራችን ጠንቅ የሚሆነው፣ ከጥቅም ውጭ የሆኑ የመንኮራኩሮች ስብርባሪ ብረታ-ብረት፣

ሌሎች ዓለማትን ለማሰስ ስለሚመጥቁ መንኮራኩሮች ፣ ስልሚላኩ የኅዋ ቴሌስኮፖች፣ በየጊዜው እናወሳለን። ይህ ገና ተጨባጭ ውጤት ያልተገኘበትን ምርምር ይሆናል የሚመለከተው። ሌላው፣ የሰው ልጅ፣ ለዕለታዊ የተቀላጠፈ የስልክና የቴሌቭዥን አገልግሎት፣ ለተሽከርካሪዎችና መርከቦችም ጉዞና አቅጣጫ ማመላከቻ(Navigation) ልዩ መንኮራኩሮችም ሆኑ ሳቴላይቶችን የሚመለከት ሲሆን እስከቅርብ ጊዜ ጥቅሙ እንጂ ውሎ-አድሮ ከተጠቀሱት መሣሪያዎች ምን ዓይነት አደጋ ሊከሠት እንደሚችል እምብዛም አልተጤነበትም ነበር። ለመገናኛም ሆነ ለሌላ፤ ለስለላም ጭምር የሚመጥቁ ሳቴላይቶች ሲበላሹ ወይም ሲያረጁ ምን ይሆናሉ?

ተክሌ የኋላ፣

ሒሩት መለሰ፣