የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 18.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ

የኢየሱስ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መታሰቢያ በዛሬዉ ዕለት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላዉ ዓለም ሲከበር ዉሏል።

የምሥራቁም ሆነ የምዕራብ አብያተ ክርስትያናት ተከታዮች በዚህ ዓመት የትንሳኤን በዓል በአንድ ቀን የሚያከብሩ በመሆኑ በተለይ በታሪክ ድርጊቱ እንደተፈጸመባት በሚገለጸዉ ኢየሩሳሌም ከመላዉ ዓለም የተጓዙ ተሳላሚዎች መገኘታቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በዓሉ በተለይም በሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በተገኙበት በእየሩሳሌም ክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ እንደተጓዘበትና ስቃይና መከራ እንደተቀበለበት በሚታመንበት መንገድ መስቀል ተሸክሞ በመጓዝ ተከብሯል ።የጀርመን የዜና ወኪል ከስፍራዉ እንደዘገበዉ ከተሳላሚዎች ብዛት የተነሳም በየዓመቱ የሚካሄደዉ የመስቀል ጉዞ በቀጭኑ የኢየሩሳሌም የጥንት ከተማ እጅግ በሰዎች የተጨናነቀ ነበር። ወደቀራኒዮ አደባባይ ለመድረስም ብዙዎች በመመሳሰሉ የሚያሳስተዉን በገበያ የተሞላ መንገድ ደጋግመዉ ሊጓዙበት ግድ ብሏቸዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥም ሃይማኖታዊ በዓሉ በከፍተኛ ድምቀት በየቤተ ክርስቲያኑ ሲከበር ዉሏል። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ወደተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋዉሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic