የሴቶች ችግር እና መፍትሄዉ | ባህል | DW | 09.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የሴቶች ችግር እና መፍትሄዉ

ሴቶች በፆታቸዉ ወደ ጎን ገሸሽ የማይደረጉበት ሁኔታ እንዴት ነ ይገመገማል? የዛሪዉ የባህል ዝግጅት አብይ ርዕስ ነዉ። የረጅም ዘመናት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ምንም እንኳ አብዛኛዉን ግዜ ከፍተኛዉን ስልጣን ይዘዉ የቆዩት ተባዕታይ ፆታ ወይም ወንዶች ቢሆኑም አልፎ አልፎ ሴቶችም ስልጣን ይዘዉ አገሪቱን ይመሩ እንደነበር ታሪካችን ያሳየናልን።

ከብዙ ጥቂቶቹ ንግስት ሳባ ወይም ማክዳ፤ እቴጌ እሌኒ፤ እቴጌ ሠብለ ወንጌል ፤ ከቅርብም ታሪኮች እቴጌ ጣይቱ እና ንግሥተ ነገሥታት ዘዉዲቱ ይገኙበታል። የለቱ ዝግጅታችን ዙርያ የሴቶች ዙርያ ያቆየናል። መልካም ቆይታ

Frauen bieten am Samstag (25.06.2011) in Gundomeskel im Gebiet Dera in Äthiopien auf dem Markt ihre Waren an. Nach langjährigem Engagement hat sich die Stiftung Menschen für Menschen aus dem Projektgebiet Dera zurückgezogen, da sich die Situation der Menschen deutlich verbessert hat. Foto: Tobias Hase dpa

ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ ሃላፊነት ተሸክመዉ አገርንም ሆነ ድርጅትን ተቋማትን እንዲመሩ ዘመናዊ ስልጣኔ እስከም አስችሏቸዋል? ከቆየዉ ባህላችን እና ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር ስናነፃፅረዉ ሴቶች በፆታቸዉ ወደ ጎን ገሸሽ የማይደረጉበት ሁኔታ እንዴት ነዉ የሚገመገመዉ?

የሴቶችን መማር እና አደባባይ መዉጣት በተመለከተ በርካታ የስነ ቃል ዓይነቶችን እናገኛለን። ለምሳሌ ሴት ከተማረች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች፤

ሴት ልጅ በማጀት ወንድ ልጅ በችሎት፤ የሴት ዘንገኛ የናት ምቀኛ፤ የሴት አስተሳሰብ ከምድጃ አይወጣም፤ የሎሌ አልቃሻ የሴት ቀዳሻ፤ ይህንን የመሳሰሉ ምሳሌያዊ አነጋገሮች የሴት ልጅን መማር እንደመልካም ነገር አለመቁጠሩን ይገልጻል ሴት ከተማረች ሕብረተሰቡ የሚጠብቅባትን ኃላፊነት በአግባቡ አትወጣም የሚል ግንዛቤም ያለ መሆኑን ከምሳሌያዊ ንግግሩ መረዳት ይቻላል። እዉን በአንድ ማህበረሰብ ዉስጥ ያለ ባህል የሴቶችን ወደጎን የሚያገል ይሆን?

በየርላንድ ነዋሪ የሆኑትና እዝያ በሚገኝ አንድ ዩንቨርስቲ መምህር የነበሩት የስነ-ሠብዕ እና የታሪክ ምሁር የሆኑት ዶ/ር ፀሃይ ብርሃነስላሴ፤ በተለያዩ አገሮች በሚገኙ ከፍተኛ ተቋማት እየተዘዋወሩ አጫጭር ኮርሶችን ይሰጣሉ። በጡረታ ላይ የሚገኙት ዶ/ር ፀሃይ፤ በአሁኑ ወቅት በሰሜናዊ ጀርመን ሃንቡርግ ከተማ በሚገኝ ዩንቨርስቲ አጠር ላለ ግዜ ኮርስ ለመስጠት ተጋብዘዉ እዚህ በጀርመን ይገኛሉ፤ ዶክተር ፀሃይ ሴቶች የጤና እንክብካቤ የማያገኙበት አጋጣሚም ጥቂት እንዳልሆነ ተናግረዋል።

Gebriemeskel, carrying water, before project took 3 hours to water point, now only 15 mins. Tigray, Ethiopia am 6.7.2009 fotografiert im Feb 2011 geladen Lizenz: http://creativecommons.org/licenses/by-nc-sa/2.0/deed.de +++CC/waterdotorg+++

ሴት ልጅ በማጀት የሚለዉን አነጋገር ሐረግ ሰፋ አድርገን ብንመለከት የመኖርያ ቤትን ሲያጠቃልል ይችላል። ስለዚህ የሴት ተግባር እንቅስቃሴ ከቤትዋ ዉጭ ሰዉ ያወቀዉ ፀሃይ የሞቀዉ መሆን እንደሌለበት በምሳሌያዊ ንግግሩ ከተላለፈዉ መልዕክት መረዳት ይቻላል። በማህበረሰብ ዉስጥ ባለ ልማድ ሴቶች ላይ የሚደርሰዉን መገለል ለመግታት ቀዳሚዉ ትምህርት ነዉ። በገጠሩ ያለዉም ሴት እርዳታ ያሻዋል ። ዶክተር ፀሃይ እንደሚሉት፤ መጀመርያ ግን የሴቶችን ፍላጎት እና ልማድ ለመረዳት የአካባቢዉን ባህል ማወቅ ያሻል ሲሉ አስረድተዋል።

ሴቶች በማግበራዊ እድገት ዉስጥ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይችሉ ዘንድ ከልዩ ልዩ ተፅዕኖዎች ነፃ መሆን እንዳለባቸዉ፤ ከነዚህ ተጽኖዎች መካከል በህብረተሰቡ ዘንድ ያለ ልማድ እንደሆነ ዶክተር ፀሃይ ይገልጻሉ። ለአገር ልማት መጫወት ያለባቸዉን ነገር እንዲፈፅሙ ለማድረግ ያለባቸዉን የባህል ተፅዕኖ ማጥናትና ማወቅ ለማስወገድም መፍትሄ ያሻል። ሴቶች በጾታቸዉ ወደጎን ገሸሽ የማይደረጉበት ሁኔታ እንዴት ነዉ ይገመገማል? በሚል ርዕስ የስነ-ሠብዕ እና የታሪክ ምሁር ዶ/ር ፀሃይ ብርሃነስላሴ ለሰጡን ቃለ ምልልስ እናመሰግናለን።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic