የሴቶች ቀንና የሴቶች ጤና | ጤና እና አካባቢ | DW | 08.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የሴቶች ቀንና የሴቶች ጤና

የሴቶች ቀን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሲታሰብ አንድ መቶ አመቱን ዘንድሮ ያዘ።

default

ለትምህርት፤ስልጠና፤ ሳይንስና ቴክኒክ እኩል መብት

በየሚኖሩበት ማኅበረሰብ በፖለቲካ፤ በምጣኔ ሃብትና በማኅበራዊ ረገድ ከፍተኛ ሚና ያላቸዉ ሴቶች መብቶቻቸዉ ከሰብዓዊ መብቶች ሳይለይ እንዲከበርላቸዉ ከተወሰነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ዛሬም ግን በየትኛዉም ዘርፍ በዉሳኔ ሰጪነት ደረጃ ላይ የሚገኙት ሴቶች ቁጥር በጣት የሚቆጠር ነዉ። ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ የሚለዉ ጥያቄያቸዉም ዛሬም ሙሉ ምላሽ አላገኘም። የተመድ የአምዓቱ የልማት ግብ የሴቶችን ጤና ለመጠበቅ በተለይ ከወሊድ ጋ በተያያዘ ትኩረት እንዲሰጠዉ አሁንም እየጠየቀ ነዉ። መቶ አመት ቢቆጠርም አፍን ሞልቶ ከዳር እስከዳር ጥያቄያቸዉ ተመለሰ ማለት አልተቻልም።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ