የሴቶች ቀንና ወጣት የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎች | ወጣቶች | DW | 09.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

የሴቶች ቀንና ወጣት የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎች

ወጣቶቹ ተሰባስበዉ ለመብት መንቀሳቀስ የጀመሩት ከ 7 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና አስተናጋጅ የነበረችው አበራሽ ሀይላይን ዓይኖች በቀድሞ ባለቤቷ ጥቃት ካጠፋ በኋላ እንደ ነበር የቡድኑ መሪ ተናግራለች።

«ወጣቶቹ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች»

መቀመጫዉን በአዲስ አበባና መቀሌ ዮንቨርስቲ ያደረገዉ የወጣት የሴቶች ጉዳይ ተሟጋች የሆነዉ የሴት ወጣቶች ቡድን ማኅበረሰቡ አካባቢዉን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ይኖርበታል ሲል ገለፀ። ዛሬ የሚከበረዉን የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት የቡድኑ ተጠሪ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሴቶችን ለማክበር አልያም ክብር ለመስጠት „March 8 „ን  መጠበቅ የለብንም ብለዋል።

 

35 ወጣት ሴቶችን ያቀፈዉና «Yellow movement» በመባል የሚታወቀዉ የሴት መብት አቀንቃኝ  ቡድን በሴትች ላይ የሚፈፀም የፆታ ጥቃት፤ ግፍና በደልን በመቃወም የሴቶችን የተለያዩ መብቶች በዘመቻ መልክ በማስተማር እንቅስቃሴዉን ከጀመረ አመታት እንደተቆጠሩ የወቅቱ የቡድኑ ተጠሬና የሴቶች መብት ተቆርሪ ወጣት ምህረት እቁባይ በርሄ ተናግራለች። በቡድን መልክ ተሰባስበዉና ለቡድኑ ስያሜ ሰጥተዉ መንቀሳቀስ የጀመሩት ከሰባት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና አስተናጋጅ የነበረችው ሆስተስ አበራሽ ሀይላይን የቀድሞ ባለቤቷ ሁለት ዓይኖችዋ ካጠፋ በኋላ እንደነበር ወጣት ምህረት እቁባይ በርሄ ተናግራለች።  

የጠረቤዛ ቀን ማለትም «ቴብል ዴይ» ሲሉ የሰየሙት ቀን ተማሪዎች ፤ ወጣቶችን በሰፊዉ የሚያገኙባቸዉን ቦታዎች በመምረጥ ስለ ፆታ ጥቃት እንዲሁም ስለጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ርዕሶችን በማንሳት ዉይይትን ጀመሩ። በመለጠቅ የደም ልገሳ መረሃግብርም አላቸዉ። አሁን በቅርቡ ደግሞ የመጽሐፍ ንባብ ክፍለ ጊዜ እንደጀመሩና በተለይ ይህ ወጣት ሴቶች የማንበብ ልማዳቸዉን እንዲያዳብሩ መሆኑ ተገልፆአል።

ስለሴቶች መብት የሚሟገተዉ ድርጅት አዲስ በቀየሰዉ መረሐ ግብር መጽሐፍ ማንበብ ልምድን ለማዳበር የሴቶች የንባብ ዝግጅት በመጀመሩ በጣም ኮርቻለሁ ስትል ወጣት ምህረት እቁባይ በርሄ ገልጻለች።

 „March 8 „ የሴቶች ቀን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ እንደማኅበረሰብ እንዴት የተሻልን ልንሆን እንችላለን ብለን ስናስብ በሴቶች አኳይም ሊከበር የሚስፈልገዉን መብት ማገዝ እንችላለን ስትል የ «Yellow movement» ወቅቱ የቡድኑ ተጠሪና የሴቶች መብት ተቆርሪ ወጣት ምህረት እቁባይ በርሄ ተናግራለች።

በጀርመን በቫይመር በተባለዉ አስተዳደር ከ 1 ነሐሴ 1918 ጀምሮ 21 ዓመት የሞላት ሴት ከወንድ እኩል በምርጫ ድምፅ የመስጠት ሕግ ተደንግጎ በሕገ-መንግስት ላይ መስፈሩን ያዉቃሉ?    

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic