የሴቶችን መብት፤ የተመድ ህግ 30ኛ ዓመት | ዓለም | DW | 18.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሴቶችን መብት፤ የተመድ ህግ 30ኛ ዓመት

በማንኛዉም መንገድ የሚፈፀመዉን አድሎና ተፅዕኖ የሚያግደዉ በተመድ የተደነገገዉ ሴቶችን የሚመለከተዉ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ዉል ዛሬ ሰላሳኛ ዓመቱን ያዘ።

default

የዑጋንዳ ሴቶች ራስ በመቻል ዉይይት

በአሁኑ ወቅትም ይህ ህግ በ186 ድርጅቱ አባል አገራት ተቀባይነት አግኝቷል። ያም ሆኖ ግርዛት፤ የግዳጅ ጋብቻ፤ ጥሎሽ፤ ለክብር ሲባል መገደል እና ሌሎች ዛሬም በዓለም ዙሪያ በሴቶች ላይ መፈፀማቸዉ አልቀረም። እንደ የዶቼ ቬለዋ ሞኒካ ግሪብለር ከበደሎቹ መካከል በመገናኛ ብዙሃን ይፋ የሚወጣዉ ጥቂቱ ነዉ፤ አንዳንዶቹ ጭራሽም አይታወቁም። ቀጣዩ ዘገባ በዑጋንዳ ዛሬም ያልተገታዉን የሚስት ዉርስን ይመለከታል፤

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ