የሴት ልጅ ግርዛትና ጀርመን | ጤና እና አካባቢ | DW | 08.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የሴት ልጅ ግርዛትና ጀርመን

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት የሆነዉ የሴት ልጅ ግርዛት ወትሮ ተንሰራፍቶ ከኖረበት ከሶስተኛዉ ዓለም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደምዕራባዊዉና ወደበለጸገዉ ዓለምም መዝለቁ እየተነገረ ነዉ።

default

...የጎጂዉ ልማዳዊ ድርጊት ሰለባ ሰቀቀን...

ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ተከታታይ ተቋም IMO እንደሚለዉ ይህ የሰለጠነዉ ዓለም ባህል አካል ያልሆነዉ ተግባር ወደአዉሮፓና ሰሜን አሜሪካ የዘለቀዉ በተበራከተዉ ስደት ምክንያት ነዉ። የሴቶችን ሰብዓዊ መብት ከመጣስ የሚቆጠረዉ ግርዛት ዛሬ ዛሬ በአፍሪቃና ሌሎች ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን በሚዘወተርባቸዉ አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን ወደጀርመንና ሌሎች የአዉሮጳ አገራትም እየተሻገረ መሆኑ ተሰምቷል። ጀርመን ዉስጥ የዚህ ችግር ሰለባዎችን በስልክ የማማከር አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል።

ናዲያ ባኤፋ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ