የሴራልዮናዊው ተገን ጠያቂ አሟሟትና አወዛጋቢው ብይን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 15.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሴራልዮናዊው ተገን ጠያቂ አሟሟትና አወዛጋቢው ብይን

ሴራልዮናዊው ኡሪ ጃሎህ በተያዘበት ክፍል ውስጥ ከነበረ ፍራሽ በተነሳ ዕሳት ሰበብ በተያዘበት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥር ሰባት ሁለት ሺህ አምስት ዓመተ ምህረት በታሰረበት ክፍል እጅና እግሩ እንደተጠፈረ ሊኖርባት የጓጓላትን ምድር እስከወዲያኛው ተሰናበተ ።

default

ከጀርመንና ከጀርመን ውጭም የበርካታ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችን ትኩረት ስቦ የቆየው ይኽው ጉዳይ ከሃያ ሁለት ወራት የፍርድ ሂደት በኃላ ባለፈው ወር በፌደራዊ ክፍለ ሀገሩ ፍርድ ቤት ብይን ተሰጥቶበታል ። ፍርድ ቤቱ በዚሁ ብይን በሰውነት ላይ ለሞት የሚያበቃ ጉዳት በማድረስ እንዲሁም ህይወት በማጥፋት ክስ ከቀረበባቸው ፖሊሶች በአንዱ ላይ የገንዘብ ቅጥት ሲወስን ሌላኛውን ደግሞ ጥፋተኛ አይደለም ሲል በነፃ አሰናብቷል ።