የሳይንስ መምህራን እጥረት በጀርመን፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 11.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የሳይንስ መምህራን እጥረት በጀርመን፣

በሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ የታወቀችው በተለይም ብዙ የሥነ -ፍጥረት ጠበብትን ለኖቤል ሽልማት በማብቃት የታወቀችው ሀገር ጀርመን፣ በመምህራን እጥረት ተቸግራለች። በጀርመን፣ መምህርነት በአሁኑ ጊዜ ያን ያህል ማራኪ የሥራ መሰክ ሆኖ አልተገኘም። የመምህራኑ አማካይ ዕድሜ በጣም ከፍ ያለ ነው። ተተኪዎች ደግሞ በፍጹም በቂ አይደሉም።

default

የጀርመን የትምህርት ሚንስትር፣ ወ/ሮ አኔተ ሻቫንና የአውሮፓው ኅብረት የምርምር ጉዳይ ኀላፊ Janez Potocnik

በመንግሥት ት/ቤቶች፣ በዚህ ረገድ የሚወጣው የወደፊት አቅድ ጉድለት የሚታይበት ነው። በወጣት መምህራን ረገድ ፣ ሥልጠናውም ፣ ልምምዱም የተሟላ አይደሉም። በመሆኑም፣ የፌደራዊው መንግሥት የትምህርት ሚንስትር ወ/ሮ አኔተ ሻቫን፣ ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው በመግልጽ፣ ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች፣ የትምህርት ብቃት ያላቸው የፊዚክስ ባለሙ ያዎች ኢንጂኔሮችና የሂሳብ ሰዎች ወደ ት/ቤቶች ተመልሰው እንዲያስተምሩ አሳስበዋል። ይህ ማሳሰቢያቸው በሌላ በኩል በሰፊው ነቀፌታ እየተሠነዘረበት ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት፣

ለኢንዱስትሪ ኩባንያ ይሠሩ የነበሩት፣ Markus Alt የተባሉት ጎልማሣ፣ ከዚያ ወጥተው አሁን በአስተማሪነት ሙያ የተሠማሩ ሲሆን፣ ቀጣሪአቸው፣ የትምህርት ሚንስትርዋ፣ ሲወተውቱ ለቆዩበት ጉዳይ ምላሽ እንደሰጠ ነው የተገመተው። የትምህርት ሚንስትር ወ/ሮ አኔተ ሻቫን፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ለተወሰነ ጊዜ የሂሳብ ፣ የፊዚክስም ሆነ የሥነ-ቅመማ ሠራተኞቻቸውን፣ ኢንጂኔሮቻቸውን ፣ አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ ለትምህርት ቤቶች እንዲያውሱ መለመን ከጀመሩ ቆይቷል። በጀርመን ሀገር፣ ከአያሌ ዓመታት በፊት አንስቶ የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪና የሂሳብ መምህራን እጥረት እንዳለ ነው የሚነገረው። መምሃራኑም አብዛኞቹ በዕድሜ የገፉ ሲሆኑ በቂ ተተኪዎች አላገኙም። በሚመጡት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሲሦ ያክሉ መምህራን ጡረታ ይወጣሉ፣ ይህም ሲሆን፣ ከየመቶው ጡረተኛ በተተኪነት የሚቀጠሩት ቁጥራቸው በ60ና 70 መካከል ብቻ ቢሆን እንጂ ከዚያ እንደማይበልጡ ነው መዘርዝር ጥናቶች የሚያስረዱት። የፍደራል ከፍላተ-ሀገር የትምህርት ሚንስትሮች ፣ የመምህራንን እጠረት መጠን በትክክል አያስረዱም። ስለሆነም በግምት ብቻ ነው መግለጽ የሚቻለው።