የሳዑዲ አረቢያ የፀረ-ሙስና  ዘመቻ  | ዓለም | DW | 24.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሳዑዲ አረቢያ የፀረ-ሙስና  ዘመቻ 

ሮይተርስ ዜና አገልግሎት ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደ ዘገበው በዓለም አቀፍ ደረጃ ስም እና ዝናን ያተረፉ የሒሳብ ነክ ወንጀሎችን የሚመረምሩ ተቋማት ለሳዑዲ መንግስት ሙያዊ ድጋፍ እየሰጡ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

የሳዑዲ አረቢያ የፀረ-ሙስና  ዘመቻ 

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት በከባድ የሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ንጉሳዊያን ቤተሰቦች፤ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት እና ቱጃሮች «ዘረፉ» ያለውን ገንዘብ እንዲመልሱ እና ራሳቸውን ነጻ እንዲያወጡ እያግባባ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ ፡፡ ሮይተርስ ዜና አገልግሎት ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው በዓለም አቀፍ ደረጃ ስም እና ዝናን ያተረፉ የሒሳብ ነክ ወንጀሎችን የሚመረምሩ ተቋማት ለሳዑዲ መንግስት ሙያዊ ድጋፍ እየሰጡ ነዉ ፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ኢትዮጵዊ  ለዶቸ ቨለ እንደገለጹት ደግሞ ምርመራው ተጠናቆ የፍርድ ሂደቱ እስኪጀመር ከአራት እስከ ስድስት ወራት ይፈጃል፡፡የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሙስና ጠርጥሮ ካሰራቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በርካታ ኩባንያ ያላቸዉ ሼሕ መሐመድ አል አሙዲ አንዱ ናቸዉ። የሪያዱ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ
 

Audios and videos on the topic