የሳዉዲ ንጉሥ ሕልፈትና ቀብር | ዓለም | DW | 23.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሳዉዲ ንጉሥ ሕልፈትና ቀብር

ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትየስዑድ አረቢያ ንጉሥ አብደላቢንአብድአዚዝአልስዑድ የቀብር ሥርዓት ዛሬ ተፈጸመ። በዘጠና ዓመታቸዉ ያረፉት የሳዉዲ ንጉሥ ታናሽ ወንድማቸዉን በአልጋወራሽነት ቀደም ብለዉ ሰይመዉ ነበር።

እሳቸዉ ራሳቸዉ በጎርጎሪዮሳዊዉ 2005ዓ,ም ነሐሴ ወር አንድ ቀን ነበር የአንድ ወገን ወንድማቸዉ ንጉሥ ፋሀድ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ነበር ወደንግሥናዉ መንበር የወጡት። ላለፉት አስር ዓመታትም ሳዉዲ ኤኮኖሚና ማኅበራዊ ስርዓቱ እየጨመረ የመጣዉን የሀገራቸዉ የሕዝብ ቁጥር ፍላጎት በሚያረካ መልኩ የሥራ እድል የሚፈeሩ የግል ዘርፎችን በማስፋፋት ወጣቶቹ ያንን ለመረከብ እንዲዘጋጁ በማድረግ በሰሩት ስራ እንደሚታወሱ ታሪካቸዉን የቃኙ ዘገባዎች ያመለክታሉ። በቦታቸዉ የተተኩት ንጉሥ ሳልማን በመካከኛዉ ምሥራቅ የሚታየዉን አለመረጋት ጨምሮ እሳቸዉ የጀመሩትን የሀገር ዉስጥ የለዉጥ ጉዞ ማስቀጠሉ ፈታኝ ሊሆንባቸዉ እንደሚችል ከወዲሁ ግምት እየተሰነዘረ ነዉ። ጂዳ የሚገኘዉ ተባባሪያችንን ነቢዩ ሲራክን በስልክ በአጭሩ አነጋግሬዉ ነበር።

ነብዩ ሲራክ/ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic