የሳንባ ሕመሞች | ጤና እና አካባቢ | DW | 18.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የሳንባ ሕመሞች

ሳንባ በተለያዩ ምክንያቶች ለሕመም የሚዳረግ የአካል ክፍል ነዉ። ለጉዳት የመጋለጡን ያህል በአግባቡ ሕክምና በመከታተል መዳንም እንደሚችል ሃኪሞች ይገልጻሉ።

የሳንባ ሕመም በብዛት እንከሰት እንደመሆኑ ምልክቱ ግልፅ ነዉ ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ፋኩልቲ የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እንዲሁም የሳንባና የፅኑ ህሙማን ተመራማሪ ባለሙያ ዶክተር ቶላ ባይሳ። ከሳንባ ሕመም ዋነኛ ምልክቶች አንዱ ደግሞ ሳል ነዉ። አንድ ሰዉ ደጋግሞ ሳል ሲይዘዉ እና ከሁለትና ሶስት ሳምንት በላይ ሲቆይበት፤ ፈጥኖ ወደሃኪም ቤት በመሄድ አስፈላጊዉን ሕክምና ማድረግ እንደሚኖርበትም ያሳስባሉ ዶክተር ቶላ።

Atmung: Atemwege

ሳንባን እንደ ኒሞኒያ/ ማለት የሳንባ ምች በመባል ሲገለፅ የምንሰማዉ፤ እንዲሁም የሳንባ መቆጣት ወይም ኢንፌክሽን፤ የመሳሰሉት ህመሞች ያጠቁታል። ታማሚዎች ከሃኪሞች እነዚህን አገላለፆች ሲሰሙ የበሽታዎቹን ምንነት ለመረዳት የሚከብዳቸዉን ያህል አንዱ ከሌላዉ እየተመሳሰለ እነሱን ብቻ ሳይሆን ለአስታማሚም ግራ የሚያጋቡበት ሁኔታ ያጋጥማል። ለበሽታ የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ የሆነዉ ይህ የአካል ክፍል በመድሃኒት ሕክምና እንደሚድን ሃኪሞች ቢያሳስቡም ብዙዎች በቤት ዉስጥ በሚደረጉ ባህላዊ ዘዴዎች መዳን እንደሚችል ይናገራሉ። የሳንባ ምች ምንድነዉ? የሳንባ ኢንፌክሽንስ? ማር፤ ነጭ ሽንኩርትና የመሳሰሉትን ከወተት ጋ መዉሰድ ሳልንም ሆነ ሌሎች የሳንባ ሕመሞችን እንደሚያድን ይነገራል? የሕክምና ባለሙያዎች ስለዚህ ምን ይላሉ? ዝግጅቱን ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic