የሳምንቱ የጀርመን ባህላዊ ጥንቅሮች | ባህል | DW | 07.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የሳምንቱ የጀርመን ባህላዊ ጥንቅሮች

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በህዝባዊት ቻይና በፔኪንግ ቲያናንመን አደባባይ በሚገኘዉ የታዋቂዉ እግዚቢሽን የጀርመናዉያኑን የስዕል እግዚቢሽን መርቀዉ ከፍተዋል፣

default

ሌላዉ ባለፈዉ ሰምወን በዚህ በጀርመን አመታዊ ምርጥ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርአትም ነበር፣ ከሙዚቃዉ ባሻገር በጃፓን በተከሰተዉ የተፈጥሮ አደጋ ሰበብ በአቶም ሃይል ማመንጫ አዉታር ላይ የደረሰዉ ከፍተኛ ጉዳት የአለም ህዝብ ሁኔታዉን ማጤን ይኖርበታል ሲል የአለም የፊልሙም መድረክ ማስጠንቀቅያ እያደረገ ነዉ። በለቱ ዝግጅታችን ሰምወኑን የጀርመን የባህል ድረ-ገጾች የዘገቡባቸዉን ርእሶች መራርጠን ልናስደምጥ አቀናብረን ይዘናል።

ባለፈዉ ሳምንት አርብ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ በቻይና ቬጂንግ ከተማ አንድ የጀርመን የስዕል ትርኢትን መርቀዉ ከፍተዋል። ይህ ታላቅ የተባለለት የጀርመናዉያን የስዕል ትርኢት ለአንድ አመት የሚዘልቅ ሲሆን ትርኢቱ በመጠርያዉ የስነ-ጥበብ መግለጫ ይሰኛል። ቻይናዉያኑ ገነተ ሰላም ብለዉ በሚጠሩት በቤጂንግ በሚገኘዉ በታዋቂዉ የTiananmen አደባባይ ላይ በሚገኘዉ ብሄራዊ ሙዝየም ዉስጥ ነዉ የጀርመናዉያኑ የስዕል ኤግዚቢሽን በመታየት ላይ ያለዉ። በዚሁ አደባባይ ላይ ከሃያ አመት በፊት የተቃዉሞ ሰልፍ በጠሩ ተማሪዎች ላይ የግፍ ጭፍጨፋ ተደርጎ ብዙ ደም ፈስዋል። ለዶቸ ቬለ ለጀርመኑ የባህል ድረ-ገጽ ከፔኪንግ ዘገባዋን ያስተላለፈችዉ ሩት ኪርሽነር እንደ ጻፈችዉ የባለ አንድ ፓርቲዉ የኤፒኪንጉ መንግስት በፔኪንግ ከተማ ካሉት አካባቢዎች ሁሉ እንደ Tiananmen አደባባይ ስልጣኑን እና ጉልበቱን ማሳየቱ ጎልቶ አይታይም ባይናት። ምክንያቱም አደባባዩን ለመጎብኘት በመጡ የከተማዋ እንግዶች እና ነዋሪዎች መካከል የታጠቁ ወታደሮች እና ፖሊሶች ሲዘዋወሩ ይታያል። ሲቪል የለበሱ የጸጥታ አስከባሪዎችም በየቦታዉ ተሰግስገዉ አካባቢዉን ይቃኛሉ። እዝያዉ አደባባይ ላይ ከሚገኘዉ ከብሄራዊዉ ሙዚየዉም ፊት ለፊት ህዝባዊትዋን ቻይና የመሰረቱት የ Mao Zedong ፎቶግራፍ በትልቁ ተለጥፎ ቆምዋል። ከፎቶዉ ፊት ለፊት በአ.አ 1989 አ.ም ወታደሮች ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎቻቸዉን ይዘዉ አፈሙዛቸዉን ወደ ተቃዋሚ ተማሪዎች ላይ የሰበቁበት ጎዳና ለጥ ብሎ ይታያል። ታድያ እዚህ ቦታ ላይ ነዉ ያለፈዉ አርብ ከዚህ ከጀርመን ከበርሊን ከሙኒክ እና ከድሪስደን ከተማ የተዉጣጡ የኪነ-ጥበብ ሰዎች የረቂቅ የስዕል ስራዎቻቸዉን ለአንድ አመት ለሚዘልቅ ትርኢት ያቀረቡት። ትምህርታዊ እና መልክት አዘል የተባለለት ይህ የስዕል ትርኢት ለአሁንዋ አዉሮጻ የነጻናት እና የሰብአዊ መብት መከበር መሰረት የተጣለበትን የተጀመረበትን ዘመን በትክክል ያስቀምጣል። የስዕል ትርኢቱ አከፋፈት ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት በድሪስደን የታሪክ እና ባህል ቅርጽ ጥበቃ ቢሮ ተጠሪ ማርቲን ሮት እንደሚሉት እግዚቢሽኑ ምንም አይነት የፖለቲካዊ መልክት የለዉም...
«ስነ-ጥበብ ምስጢራዊ የሆነ ሁለት አይነት መልክትን ያዘለ ትርጉም ሊኖረዉ ይችላል። እዚህ ላይ ግን በጥልቅ ገብቶ መመርመር እና ማየት ያስፈልጋል። እኛም በዚህ እግዚቢሽን ባቀረብነዉ ስነ ጥበባዊ ስራ በአንድ ርዕስ የተለያዩ መልክቶችን ማሳየት ነዉ የፈለግነዉ። በዚህም ሁሉም ተመልካች ያቀረብነዉን በስዕል የተደገፈ መልክት ይረዳል የሚል ግምት የለንም። በጀርመንም ቢሆን ሁኔታዉ ከዚህ አይለይም»
በእግዚቢሽኑ የቀረቡት ስዕሎች ዉጫዊ ዉበታቸዉ ብቻ ሳይሆን ዋናዉ ጉዳይ በአስራ ስምንተኛዉ ክፍለ ዘመን የዘመናዊ ሳይንስ አመጣጥ እና የመገናኛ ብዙሃን ምስረታ፣ በአዉሮጻ ነጻ ሃሳብን የመግለጽ ልዪ ልዪ ዕዉቀትን ይዞ የመገኘት መሰረት መጣሉንም ያንጸባርቃል። የእዚህ እግዚቢሽን አዘጋጆች ያቀረቡት የስእል እግዚቢሽን በቻይና መልክቱ ደርሶ የዉይይት መድረክ ይከፈታል ብለዉ ያምናሉ። የቻይናዉ ታዋቂ የኪነጥበብ ሰዉ Ai Weiwei ግን ቻይና ዉስጥ በአሁኑ ወቅት ይህ እድል አይኖርም።
«አዉሮጻዉያን በአስራ ሰባተኛዉ እና በአስራ ስምንተኛዉ ክፍለ ዘመን፣ የሰብአዊ መብት እና ነጻ ሃሳብን የመግለጽ ጉዳዪችን ቢያመጡም ቅሉ እስከ ዛሪ ቻይና ይህ ጉዳይ መቀበል አልቻለችም። እነዚህ የስዕሎች በቻይና መንግስት ተቀባይነትን አግኝተዉ በአገሪቱ ዉስጥ ለእይታ ቢቀርቡም ስነ-ጥበባዊ ምስጥሩን በተመለከተ ሃሳቡን ለመግለጽ የዉይይት መድረክ መክፈት አይፈቀድም»

China Kunst Künstler Ai Weiwei verhaftet


Ai Weiwei በፔኪንግ ስለተከፈተዉ ስለ ጀርመናዉያኑ የስዕል እግዚቢስን ይህን ሃሳቡን ለጋዜጠኛዋ ከገለጸ በኳላ ያለፈዉ እሁድ ወደ ሆንግ ኮንግ ለማምራት በቤጂንግ አለም አቀፍ አየር ጣብያ በፖሊች ተይዞ መወሰዱ ታዉቋል። ይህ የተነገረዉ አይ ቫይ ቫይ የስነ ጥበብ ስራዎቹን ለማስፋት በበርሊን አንድ ስቱድዮ እንደሚከፍት ከተነገር ከአንድ ቀን በኳላ ነበር። አይ ቫይ ቫይ በበርሊን ስዕል ስራዎችን ስቱድዮ ከፍቶ ለመቀጠል የፈለገዉ በያዝነዉ በአዉሮጻዉያኑ አመት መጀመርያ ላይ የቻይና መንግስት የሚሰራበትን የቤጂንጉን ስቱድዮ በማሸጉ ነበር። አይ ቫይ ቫይ በጥበባዊ ስዕሎቹ በተለይ እ.አ 2008 አ.ም በቻይና ሲሻዉን ሰማንያ ሽህ ህዝብ ያለቀበት የመሪት መንቀጥቀጥ፣ የትምህርት ቤት ህንጻዎች በአግባቡ ባለ መገንባታቸዉ የብዙ ህጻናት ህይወት መጥፋት አንዱ ምክንያት መሆኑን በማስቀመጥ የህዝባዊ ቻይናን መንግስት በመተቸት ተቃዉሞዉን በግልጽ አስቀምጦአል። ሌላዉ በቅርቡ በመካከለኛዉ እና በሰሜን አፍሪቃ የያስሚኑ አብዮት ሲዛመት በቻይናም በድብቅ የሚንቀሳቀሱ የመንግስት ተቃዋሚ ቡድኖች ጥሪ በማድረግ ላይ ሳሉ መንግስት ተከታትሎ አክሽፎባቸዋል። በሆንኮንግ የሚገኘዉ የቻይና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት እንደሚያትተዉ ከየካቲት ወር ጀምሮ ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ቻይና መንግስት ተቃዋሚዎች ቻይና ዉስጥ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። የዶቸ ቬለዉ የባህል ድረ-ገጽ በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ በፔኪንግ ስለ ጀርመናዉያኑ የስዕል እግዚቢሽን እና ቻይናዊዉ የኪነጥበብ ሰዉ መታሰሩን በተመለከተ ሰፋ ያለዉን ዘገባ አስፍሮአል።

Deutschland Musik Echo 2011 Sängerin Lena Meyer-Landrut


ሌላዉ ባለፈዉ ሰምወን በጀርመን ዋና ከተማ በበርሊን የተካሄደዉ አመታዊዉ በአገር ዉስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የሆኑ የምርጥ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ አሸናፊ የሽልማት ስነ-ስርአት ተካሄዶአል። እዚህ ስነ-ስርአት ላይ በጀርመን አዲስ ከመጡ የአገር ዉስጥ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ መካከል ባለፈዉ አመት የሃምሳ አምስተኛዉን የአዉሮጻ አገሮች የሙዚቃ ዉድድር ጀርመን የአሸናፊነትን ቦታ እንድትጨብጥ ያደረገችዉ ሌና ማየር ላንድ ሩት ሁለት ሽልማትን አግኝታለች። የአስራ ዘጠኝ አመትዋ ሌና በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርአት ላይ በመጭዉ ግንቦት ወር ጀርመን በምስታናግደዉ በሃምሳ ስድስተኛዉ የአዉሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር ላይ ይዛ የምትቀርበዉን ሙዚቃም በሽልማት ስነ-ስርአቱ ላይ ለነበረዉ ታዳሚ አቅርባለች። ሌላዉ በአለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ በመሆን ታዋቂዉ እንግሊዛዊ ሮቢ ዊሊያምስ የሚገኝበት የእንግሊዙ ቴክ ዛት የተሰኝዉ የወንዶች የሙዚቃ ቡድን ሽልማቱን አግኝቶአል። በዚሁ አመታዊ የምርጥ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርአት በጀርመን ተወዳጅ የሆኑ የባህል ሙዚቃን አቀንቃኝ እና ቀማሪዎች በተለያየ ደረጃን ሽልማትን አግኝተዋል። በጀርመን ለደራስያን ለከያንያን እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዩች ላይ ለሚተገብሩ ግለሰቦች በየአመቱ ለሰሩት ጥሩ ስራ አገራቸዉን ለአስተዋወቁበት ተግባር ሽልማትን የመስጠት እና የማመስገን ባህል የተለመደ ነዉ።»

Deutschland Musik Band Tokio Hotel in Oberhausen


ሌላዉ ቶክዮ ሆቴል በመባል የሚታወቀዉ ወጣት የጀርመናዉያኑ የሙዚቃ ቢድን በአለም ታዋቂ እና ተወዳጅ የሙዚቃ ቡድን መሆኑን በመግለጽ የጀርመኑ የባህል ድረ-ገጽ አራት ወጣትን ስላቀፈዉ እና ቶክዮ ሆቴል ተብሎ ስለሚጠራዉ የሙዚቃ ቡድን በገጹ አትቶአል። ቶክዮ ሆቴል የተሰኝዉ አራት ወጣት ጀርመናዉያንን ያቀፈዉ የሙዚቃ ቡድን እ.አ 2007 አ.ም ጀምሮ በጀርመን እና ጀርመንኛ ቋንቋን በሚናገሩ የአዉሮጻ አገራት ታዋቂነትን ማግኘት ጀምሮ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዘኛ ቋንቋ በማዜም ታዋቂነታቸዉ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጠነከረ መምጣቱ እና እስካሁን ስድስት ሚሊዮን የሙዚቃ አልም መሸጣቸዉ ተገልጾአል።
ከሙዚቃ ባሻገር የልዪ ልዪ ማህበረሰብ ቋንቋዎችን ማወቅ የተለያዩ ባህሎችን መገንዘብ መሆኑም ተገልጾአል። ጀርመናዊቷ የስነ-ጽሁፍ ኖቤል ተሸላሚ ሄርታ ሙለር፣ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገረዉ ሃሳብ እና አመለካከት እንደ ባህሉ የተለያየ ነዉ ሲሉ መግለጻቸዉን በማተት የዶቸ ቬለዉ የባህል ድረ-ገጽ ዘገባዉን ይቀጥላል። የሜቂዶንያ ተወላጅ ራትካ ዞቭስካ የሜቂዶንያ የጀርመንኛ የስፓኝ የሰርብ የእንግሊዝ እና የግሪክን ቋንቋ በአጠቃላይ ስድስት የተለያዪ ቋንቋዎችን ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ። ቋንቋዉን በማወቃቸዉም ቋንቋዉን በሚናገሩት ማህበረሰቦች ዘንድ ሃሳባቸዉን በደንብ መግለጽ ስለሚችሉ እና የማህበረሰቡንም ባህል ስለሚረዱ አገራቸዉ እንዳሉ ሁሉ እንደሚሰማቸዉ ተናግረዋል። »

Deutsch als Fremdsprache an der Uni Siegen


የጀርመንኛ ቋንቋን አገራቸዉ የተማሩት የመቂዶኒያዋ ተወላጅ ቋንቋን የመማር ፍቅርና ተሰጦም እንዳላቸዉ አልደበዉም። በሃያ አንድ አመታቸዉ ጀርመን አገር መተዉ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርትን በዪንቨርሲ ደረጃ አጠናቀዉ በአሁኑ ግዜ እዚሁ በጀርመን አገር የጀርመኝኛ ቋንቋ አስተማሪ ሆነዉ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ራትካ ዞቭስካ ቋንቋን ከማስተማር ጎን ለጎን የኔዝርላንድ የፖርቱጋል የአርብኛ እና የሂብሩ ቋንቋን በመማር ላይ በመሆናቸዉ የጀርመኑ የባህል ድረ-ገጽ ልዪ ልዪ ቋንቋን ማወቅ ባህልን ህብረተሰብ በቀላሉ ለመረዳት ዋና መሳርያ መሆኑን በመግለጽ ዘገባዉን ይደመድማል።

አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ