1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት በየጣቢያዎች ይፋ ተደርጓል

ሐሙስ፣ ኅዳር 11 2012

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ውጤቶች ዛሬ በየምርጫ ጣቢያዎች ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔውን የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ከ24 እስከ 48 ሰዓት ባለው ጊዜ እንደሚያስታውቅ ትላንት ምሽት ቢገልጽም እስካሁን ድረስ ውጤቱን አላሳወቀም።

https://p.dw.com/p/3TUSh
Äthiopien Sidama Referendum
ምስል Getty Images/AFP/M. Tewelde

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤቶች በየጣቢያዎች ይፋ ተደርገዋል

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ጊዜያዊ ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎች ተለጥፎ መራጮች ዛሬ ከንጋቱ ጀምሮ ውጤት እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ውለዋል። ለዚሁ አላማ ተተክለው የነበሩ ድንኳኖችም መነሳት ጀምረዋል። 

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የሃዋሳ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ “ውጤቱ ምንም ይሁን ምንም፤ ዋናው ጉዳይ ሰላም እና ተቻችሎና ተከባብሮ መኖር በመሆኑ ምንም ስጋት ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል። በትላንትናው ዕለት የተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በሰላም በመጠናቀቁም ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ሰለሞን ሙጬ

ተስፋለም ወልደየስ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ