የሱዳኖች ድርድር ና የአፍሪቃ ህብረት | አፍሪቃ | DW | 26.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሱዳኖች ድርድር ና የአፍሪቃ ህብረት

የሰሜንና ደቡብ ሱዳንን የሠላም ድርድር ማስቀጠል የአፍሪቃ ህብረት ዋነኛ ትኩረት መሆኑ ተገለፀ ። በሌላም በኩል ሁለቱን ሱዳኖች ለማግባባት የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ዛሬ ካርቱም ገብተዋል።

South African President and Chairperson of the African Union Committee on Libya, Jacob Zuma, left, talks with Ramtane Lamamra, African Union Commissioner for Peace and Security in Addis Ababa, Ethiopia, Friday, Aug. 26, 2011 during a conference on Libya. (Foto:Elias Asmare/AP/dapd)

ራምታን ላማምራ ና ጄኮብ ዙማ

ሰሜንና ደቡብ ሱዳን አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄዱት የሠላም ውይይት ያለ ውጤት ቢያበቃም ንግግሩ በአዲስ መልክ እንደሚቀጥል የአፍሪቃ ህብረት አስታወቀ። የአፍሪቃ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሽነር ራምታን ላማምራ ዛሬ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት የሁለቱን ወገኖች የሠላም ድርድር ማስቀጠል የህብረቱ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አስታውቀዋል። በሌላም በኩል ሁለቱን ሱዳኖች ለማግባባት የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ዛሬ ካርቱም ገብተዋል። አቶ ኃይለ ማርያም ለዚሁ አላማ ነገ ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚሔዱም የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ኮሚሽነር ላማምራን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች