የሱዳኖች ዉዝግብና የአብዬ ግዛት | አፍሪቃ | DW | 14.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሱዳኖች ዉዝግብና የአብዬ ግዛት

ጦር ያማዘዛቸዉን ጠብ ለማስወገድ ባለፈዉ መስከረም ተስማምተዉ ነበር።አዲስ አበባ ላይ ያደረጉት ስምምነት ዝርዝር ይዘት፥ የገቢራዊነቱ እንዴትነት አስተንትኖ ሳያበቃ አሁን እንደገና ሌላ ዉዝግብ፥ ጭቅጭቅ ገጥመዋል።ምክንያት አብዬ ግዛት።

(FILE) A file picture dated 19 January 2010 shows Sudanese President Omar el Bashir (R) and First Vice President and President of the Government of Southern Sudan, Salva Kiir Mayardit (L), participating in celebrations marking the 5th anniversary of the signing of the Comprehensive Peace Agreement (CPA) in Yambio, Sudan. Omar el Bashir has won the country's first multiparty elections in 24 years, election officials said on 26 April 2010. The polls are supposed to usher in a new era of democracy in Sudan, which is recovering from a decades-long civil war between the north and south. EPA/TIM MCKULKA - UNMIS - HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++

የሁለቱ ሱዳኖች መሪዎች


የሰሜን እና የደቡብ ሱዳን መንግሥታት በአብዬ ግዛት ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ እንደገና አገርሽቷል።ሁለቱ ሱዳኖችን የግዛቲቱን የወደፊት አስተዳደርን በድርድር እንዲወስኑ የአፍሪቃ ሕብረት የቆረጠዉ ቀነ-ገደብ ባለፈዉ ሳምንት አብቅቷል።የሁለቱ ሱዳኖች ተደራዳሪዎች ግን እስካሁን ከስምምነት አልደረሱም።የአፍሪቃ ሕብረት ባለፈዉ ጥቅምት በወሰነዉ መሠረት የካርቱምና የጁባ ባለሥልጣናት በአብዬ ሰበብ የገጠሙትን ዉዝግብ ለማስወገድ ካልተስማሙ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚመራዉ አስታዉቆ ነበር።ሰሜን ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአብዬን ጉዳይ ይወስን መባሉን አጥብቃ ተቃዉማለች።

የሰሜን እና የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች፥የድርድራቸዉ ሒደት-በዉዝግባቸዉ ንረት፥ የስምምነታቸዉ ዉል፥ በግጭታቸዉ ግመት፥ የመግባባታቸዉ ድምቀት በመጣላታቸዉ ፅልመት ሲዳፈን እነሆ-ደቡብ ሱዳን መንግሥት ሆና የሁለተኛ ዓመት ጉዞዋን አጋመሰች።የጠብ-ስምምነት፥ የግጭት-ድርድር፥ የሰላም-ጦርነቱ ጉዞ-ምልሰት ግን አሁንም አልተለወጠም።

ደቡብ ሱዳኖች በሰሜኖች ይሁንታና ስምምነት ጁባ ላይ መግሥት ከመሠረቱ በኋላ ከድሮ ጠላቶቻቸዉ ጋር ጦር ያማዘዛቸዉን ጠብ ለማስወገድ ባለፈዉ መስከረም ተስማምተዉ ነበር።አዲስ አበባ ላይ ያደረጉት ስምምነት ዝርዝር ይዘት፥ የገቢራዊነቱ እንዴትነት አስተንትኖ ሳያበቃ አሁን እንደገና ሌላ ዉዝግብ፥ ጭቅጭቅ ገጥመዋል።ምክንያት አብዬ ግዛት።

Hundreds of southern Sudanese take part in a demonstration against northern Sudan's military incursion into the border town of Abyei in the southern capital of Juba, Sudan, on Monday May 23, 2011. The northern Sudanese military took effective control of hotly contested Abyei on Saturday night, chasing out southern forces and shelling the United Nations compound, as southern Sudan prepares to secede from the north on July 9th, (AP Photo/Pete Muller)

ደቡብ ሱዳን ሰልፍ «አብዬ የኛ ናት»የማንነቷ ያለዉን፥ በኢትዮጵያ ጦር የምትጠበቀዉን ያችን አዋሳኝ ግዛት አንዳዶች ለሁለቱ ሱዳኖች እጅግ ሥልታዊ ጠቀሜታ ያላት ይሏታል።ሌሎች ለም።ሁለቱም ሱዳኖች-አንዳቸዉ ከሌላቸዉ ሌላ ነገር-ለማግኘት የግዛቲቱን ጠቃሚነት ያወሳሉ።የሱዳን ጉዳይ አጥኚዉ ሪቻርድ ባርልትሮፕስ እንደሚሉት አብዬ-የሚባልላትን ያክል ጠቃሚ አይደለች።

«ችግሩ ሁለቱም መንግሥታት ወይም ወገኖች ለብዙ አብዬን ዉድ ዕቃ ሰጥቶ ርካሽ እንደመቀበያ የመደራደሪያ ማስመሰያ የመጠቀም አዝማሚያ ማሳየታቸዉ ነዉ።ግን የሁለቱ ሱዳኖች መንግሥታት ከአብዬ የሚያገኙት ጥቅም ምንም ወይም በጣም ጥቂት መሆኑ ነዉ ምፀቱ።ሥለ አብዬና ከአብዬ የሚወጣዉ ጫጫታና ሙቀት ከትንሺቱ ግዛትና ጥቅሟ ጋር ሲነፃፀር አለቅጥ የበዛ ነዉ።»

በርግጥም የካርቱምና የጁባ መንግሥታት በየፊናቸዉ እንደሚፎክሩት አብዬን ማጣን ሁሉን ማጣት ነዉ።የሰሜን ሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት እንኳን የአብዬን ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይወስን ማለት ጦርነት ከማወጅ የሚቆጠር ነዉ።

ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ሁለቱ ሱዳኖች አብዬን ለመቆጣጠር እንዲሕ የተማረሩት ግዛቲቱ ከሥልታዊ ጠቀሜታዋ፥ ከለምነቷ በላይ በነዳጅ ዘይት ሥለበለፀገች ነዉ።አብዬ ኖረዉ አብዬን ለሚያዉቋት ለባርልትሮፕስ ግን ይሕም ዉሸት ነዉ።

«ይሕ እዉነት አይደለም።ትክክል አይደለም።ዘ-ሔግ የሚገኘዉ ዓለም አቀፍ የድንበር አካላይ ፍርድ ቤት ከብዙ ዓመታት በፊት በወሰነዉ መሠረት በአብዬ መልከዓ ምድራዊ የግዛት ክልል የሚገኘዉ ነዳጅ በጣም ትንሽ ነዉ።አንድ ቢበዛ ሁለት የነዳጅ መስክ ብቻ።ሥለዚሕ ግዛቲቱ በነዳጅ ዘይት የበለፀገችም አይደለችም።»

ሁለቱ ሱዳኖች አብዬን አሳብበዉ የሚወዛገቡ፥ የሚፏክሩ፥ የሚዛዛቱበት ምክንያት ግን አላቸዉ።


Photo: Abandoned hut in Abyei, Verlassene Hütte in Abyei Description: Small abandoned hut in Abyei, Southern Sudan/ Die Bewohner dieser Hütte sind aus ihrem Dorf in Abyei , Süd Sudan, geflohen. Stichworte: Sudan, Süd Sudan, Guerilla, bewaffnet, Überfall, Dorf, Flüchtlinge, Abyei Date: March, 2011 Location: Abyei, Southern Sudan Photo credit: Guy Degen Photographer contact: guy.degen@dw-world.de

ከየአብዬ መንደሮች

«በሁለቱ ሱዳኖች መካካል ያለዉ መሠረታዊ ጉዳይ የነዳጅ ዘይት ምርትና ሽያጭ ነዉ።የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ምርት እና በሰሜን በኩል ወደ ዉጪ መላኩ።ይሕ ነዉ የሁለቱ ሱዳኖች ትልቅ ልዩነት።ከዚሕ በተጨማሪ የፀጥታ ጉዳይ፥ የጋራ ትብብርና የድንበር ጉዳዮች አሉ።በነዚሕ በተለይ መጀመሪያዉ ጉዳይ ነዉ ሁለቱ ሱዳኖች መስማማት ያቃታቸዉ።»

በአብዬም ተሳሰበበ፥ በደቡብ ኮርዶፏን ወይም በሌላ ስምምነቱ-በግጭት፥ ድርድሩ በዉዝግብ፥ ሠላሙ በጦርነት የመናጡ ዑደት የሚቆምበት ብልሐት በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ለባርልትሮፐስ ጥሩ ጥያቄ።

«ጥሩ ጥያቄ ነዉ።እንደሚመስለኝ ሁለቱ መንግሥታት ሊያተኩሩበት የሚገባዉ ዋና ጉዳይ የደቡብ ሱዳንን ነዳጅ ማምረትና በሰሜን ሱዳን በኩል ወደ ዉጪ መላኩን መቀጠል ነዉ።ከነዳጅ ሽያጩ ደቡብ ሱዳን ጠቀም ያለ፥ ከአገልግሎቱ ደግሞ ሰሜን ሱዳን በመጠኑም ቢሆን የሚያገኙት ገቢ የገረረዉን የሁለቱን ሱዳኖች ግንኙነት ለማለስለስ ይጠቅማል።ዉጥረቶችን አርግቦ በሌሎች ጉዳዮችን የሚደረጉ ድርድሮች እንዲሰምሩ ይረዳል።»

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰAudios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች