የሱዳን እርስበርስ ጦርነትና የግብረሠናይ ድርጅቶች ስሞታ | ኤኮኖሚ | DW | 13.05.2004
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የሱዳን እርስበርስ ጦርነትና የግብረሠናይ ድርጅቶች ስሞታ

አሁን ያሜሪካው ውጭጉዳይ መሥሪያቤት ዋሽንግተን ውስጥ በሰጠው መረጃ መሠረት፣ ፳፩ ዓመታት ያስቆጠረው የሱዳኑ እርስበርስ ጦርነት እንዲቆም የተደረሰው የሰላም ስምምነት መጨረሻ እርከን እምዲተገበር ለመርዳት አንድ የአሜሪካውያን ዲፕሎማቶች ቡድን ወደ ኬንያ አምርቷል። እንደሚታወቀው፣ ለሱዳን የሰላሙ ስምምነት የተደረሰው፣ ከኬንያ ርእሰከተማ ናይሮቢ በስተምዕራብ በኩል በ፩፻ ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ናይቫሻ በተባለው ቦታ ነው። ለአፍሪቃ ጉዳዮች

ሱዳናውያን ስደተኞች

ሱዳናውያን ስደተኞች

�ላፊነት ባላቸው በአሜሪካዊው ረዳት ውጭጉዳይ ሚኒስትር ቻርልስ ስናይደር የሚመራው የዲፕሎማቶቹ ቡድን ሁከት ባለበት በሱዳን ክፍለሀር ዳርፉር ሰብዓዊው መብት ስለሚጣስበትም ሁኔታ ነው ከሱዳኑ መንግሥት ጋር ውይይት የሚያካሂደው።

የሰብዓዊ መብት ማስጠበቂያ ቡድኖች በየጊዜው የሚያቀርቡት ስሞታ፣ የሱዳኑ መንግሥትና ከርሱ ጋር የሚተባበሩት ዓረብ-ታጣቂዎች በጥቁሮቹ የዳርፉር ነወሪዎች ላይ የጎሳ ጠረጋ ርምጃ እንደሚያካሂዱ፣ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችንም ከየመኖሪያ ቦታቸው እንዳባረሩ ያመለክታል። ሱዳን ይህንኑ ክስ ታስተባብላለች።

ኬንያ ውስጥ ሲካሄድ በቆየው የሰላም ፍለጋ ውይይት ላይ ዋንኞቹ ተደራዳሪዎች--ሱዳናዊው ምክትል ፕሬዚደንት ዓሊ ኦስማን ሞሐመድ ታሃ እና የዋነኛው አማጺ ቡድን/ማለት የሱዳን ሕዝባዊ ሐርነት ጦር መሪ ጆን ጋራንግ--አሁን የሚታይባቸውን የሐሳብ ልዩነት ለማስወገድና አስማሚውን የመጨረሻ እልባት ለማስገኘት ነው አሜሪካውያኑ ዲፕሎማቶች አሁን ሙከራ የሚያደርጉት።

የሱዳን ሕዝባዊ ሐርነት ጦር በተሰኘው እንቅስቃሴ ሥር ከ፳፩ ዓመታት በፊት ጅምረው በምዕከላዊው መንግሥት አንፃር የሚዋጉት ደቡብ ሱዳናውያን፣ ለዚያው አካባቢያቸው የእኩልነትን መብት ለማስከበር፣ ደቡባውያኑ የሱዳን ግማድ እንደሆኑ ለመቆየት ይፈልጉ ወይም አይፈልጉ እንደሆን የምርጫውም መብት እንዲሰጣቸው የሚታገሉ መሆናቸውን ነው የሚያስገነዝቡት።

ሱዳን ውስጥ አሁን በተለይ አሳሳቢ ሆኖ የሚታየው በምዕራብ ሱዳን በክፍለሀገር ዳርፉር ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ ነው። የሱዳኑ መንግሥት ቢዚያው አካባቢ ለተጨነቁት አእላፍ ተፈናቃዮች አስፈላጊው ርዳታ እንዳይዳረስ እንቅፋት ይሆናል በማለት አሁን በርካታ ግብረሠናይ ድርጅቶች ናቸው ስሞታ የሚያቀርቡት። ከእነዚሁ መካከል አንዱ የሆነው የጀርመኑ የዓለም ረሃብ መከላከያ ድርጅት/ዶይቸ ቬልትሁንገርሂልፈ እንደሚለው፥ ለአእላፉ ስደተኞች ለማደል ፩ሺ፩፻ ቶን የመባልእት ርዳታ ዝግጁ ቢያደርግም፣ የሱዳኑ መንግሥት በሩን ዘግቶበታል። መግብረሠናይ ድርጅቶቹ ግምት መሠረት በዚያው የቀውስ አካባቢ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ተፈናቃዮች ናቸው አጣዳፊው ርዳታ የሚያስፈልጋቸው። ዶይቸ ቬልትሁንገርሂልፈ ቦን ውስጥ የሰጠው መግለጫ እንደሚያመለክተው ከሆነ፣ ከዳርፉር ተፈናቃዮች መካከል ፩፻ሺ የሚደርሱቱ ወደ ጎረቤት ቻድ ሲሸሹ፣ አንድ ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ የሱዳኑ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው መጠለያ ማዕከላት ውስጥ ነው የተከማቹት። አሁን ደግሞ በሱዳን ደቡብ-ሥራቅም አካባቢ የተፈጠረው የስደተኞች መከራ እየተባባሰ እና የዳርፉሩን ቀውስ ያህል እየከፋ መገኘቱን የተባ መ ድርጅት በጥብቅ ነው የሚያስጠነቅቀው።