የሱዳን አብዮት እና የተቃዋሚዎች አጣብቂኝ | አፍሪቃ | DW | 01.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የሱዳን አብዮት እና የተቃዋሚዎች አጣብቂኝ

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታኅ አል-ቡርሐንን ፎቶግራፍ የያዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በትናንትናው ዕለት በኻርቱም አደባባይ ወጥተው ሥልጣን ለተቆጣጠሩ ሹማምንት ድጋፋቸውን ገልጸዋል። በዕለተ-አርብ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ አል-በሽርን ከሥልጣን ያወረደው የሱዳን አብዮት የገባበትን ኹነኛ ቅርቃር የሚያሳይ ሆኗል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:50

የሱዳን ባለሙያዎች ማኅበርን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመሩት እና ለወራት የዘለቀው ተቃውሞ ወታደራዊ ሹማምንቱ ሥልጣናቸውን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ይሻሉ። ተቃዋሚዎች እና የሽግግር መንግሥቱን የሚመሩት ወታደራዊ መኮንንኖች ምርጫ እስኪካሔድ ድረስ አገሪቱን ለመምራት ስለሚቋቋመው መንግሥት እስካሁን መስማማት ተስኗቸዋል። ግብፅ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን የመሳሰሉ አገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር ገፋ ሲልም በሱዳን የተከሰተው ድንበር ተሻግሮ በፖለቲካቸው ጫና እንዳያሳድር እጃቸውን አስገብተዋል። ይልማ ኃይለሚካኤል ተጨማሪ ዘገባ አለው።

ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic