የሱማሊያ የሽግግር መንግስት የከፈተው ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 05.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሱማሊያ የሽግግር መንግስት የከፈተው ጉባኤ

የሱማሊያ የሽግግር መንግስት ህጋዊ የስልጣን ዘመን ከአንድ ወር በፊት ነበር የሚያበቃው። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ሼክ ሸሪፍ አህመድ የሽግግር መንግስታቸዉን የህጋዊነት ጊዜ ለአንድ አመት ሊያራዝም የሚያስችለዉን ዉል ካምፓላ ላይ ባለፈዉ ሰሞን ተፈራርመዋል።

default

ይህ ሁኔታ ግን ሁሉንም ወገኖች እኩል አላስደሰተም። በጦርነት እና በረሀብ የተጠቃችው አገር ሶማሊያ የተሻለና የተረጋጋ መንግስት ለማቋቋም እንድትበዋ ከትናንት ጀምሮ ለ ሶስት ቀናት የሚቆይ ጉባኤ ሞቃድሾ ላይ ተከፍቷል። ልደት አበበ ሞቃዲሾ የሚገኘውን የዶይቸ ቬለ ኪስዋኺሊ ክፍል ዘጋቢ ፤ ሁሴይን አዌይስን በጉዳዩ ላይ አነጋግራ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች። ልደት አበበ

Audios and videos on the topic