የሱማሊያ ስደተኞችን ለመመለስ የገንዘብ ማሰባሰብ | አፍሪቃ | DW | 22.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሱማሊያ ስደተኞችን ለመመለስ የገንዘብ ማሰባሰብ

የሱማሊያ ስደተኞችን ከጎረቤት ኬንያ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም የሚያስችል የገንዘብ ርዳታ ለማሰባሰብ ቤልጂየም ብራስልስ ውስጥ ረቡዕ፣ ጥቅምት 10 ቀን፣ 2008 ዓም በተጠራ የለጋሾች ስብሰባ ከ105 ሚሊዮን ዩሮ በላይ መገኘቱ ተገልጧል። ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱት በፍቃዳቸው እንደሚሆንም የተመድ አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:49 ደቂቃ

የሱማሊያ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ

የለጋሾችን ስብሰባ የጠራው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ (UNHCR) ከአውሮጳ ኅብረት ጋር በመተባበር መሆኑ ተዘግቧል። በዚህ የሱማሊያ ስደተኞችን ወደሀገራቸው መመለስን እና ማቋቋምን በተመለከተው ስብሰባ የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ እና የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ ከ40 የሚበልጡ ሃገራት ተወካዮች ተገኝተዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤስብሰባውን ተከታትሎ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሮልናል።

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic