የሰዎች ለሰዎችና «በጋራ ለአፍሪቃ» | ኢትዮጵያ | DW | 25.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰዎች ለሰዎችና «በጋራ ለአፍሪቃ»

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የልማት ተግባራትን የሚያከናዉነዉ በጎ አድራጎት ድርጅት ሰዎች ለሰዎች ማለትም Menschen für Menschen ከያዝነው ዓመት ጥር ወር አንስቶ ከሌሎች አፍሪቃ ዉስጥ በእርዳታና እና ልማት የሚሳተፉ ድርጅቶች ጥምረትን ተቀላቀለ።

default

የሰዎች ለሰዎች አምባሳደር የሆነችዉ ወጣቷ ሞዴል ሣራ ኑሩ ላለፉት አምስት ዓመታት ድርጅቱ ስላከናወናቸዎ ፕሮጀክቶች ስትገልፅ፤

«እኛ ባለፉት አምስት ዓመት የሚያስደንቅ እንቅስቃሴ ነው ያደረግነው። ከጀርመናዉያን ተማሪዎች ከተዋጣው ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ዩሮ በደገሌ ትምህርት ቤት አስገብቶል፤ ሁለተኛውም ትምህርት ቤት ግንቦት ላይ ይመረቃል፤ ሦስተኛው በመገባት ላይ ይገኛል። እንግዲህ ከሦስት እስከ አራት በሚሆኑ የትምህርት ዓመታት ውስጥ ሦስት ትምህርት ቤቶች ከጀርመን ተማሪዎች በተገኘ ርዳታ የተሰሩ መሆናቸዉ ነዉ። በአጠቃላይ ሰዎች ለሰዎች ከ30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሠራ ይገኛል። ከሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል የመንገድ ሥራን፣ ሆስፒታል ግባታን እንዲሁም የውሃ ቁፋሮ ይገኙበታል። እንደ እኔ ግምት ጥሩ ሥራ ተሰርቶል ብዬ አስባለሁ።»

Sara Nuru Gewinnerin Germany's next Top Model

ከ20 በላይ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በህብረት በመሆን «በጋራ ለአፍሪቃ» በሚል አላማ አፍሪቃ ውስጥ የእርዳታ እና የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ። ሰዎች ለሰዎች የግንኙነት መረቡን በመዘርጋት ከነዚህ ድርጅቶች ጋር ካለፈዉ ጥር ወር ጀምሮ ተጣምሮ በመሥራት ላይ ነው። የጀርመኑ ፕሬዝዳት ዮአኺም ጋውክ አፍሪቃ ውስጥ የሚሰሩት ድርጅቶች የበላይ በመሆን ያግዛሉ። ድርጅቱን በአምባሳደርነት የምታገለግለዉ ሣ«በጋራ ለአፍሪቃ» የተሰኘዉን ጥምረት የተቀላቀለዉሰዎች ለሰዎች ፕሮጀክቶችበጥምረቱ አምባሳደሮች ሰሞኑን እንደሚጎበኝ አመልክታለች።

«እንደእኔ ሰዎች ለሰዎች «በጋራ ለአፍሪቃ» የተሰኘዉን ጥምረት መቀላቀሉ ጥሩ ነዉ። ጥምረቱ ዉስጥ በአሁኑ ጊዜ በመላዉ አፍሪቃ ውስጥ የሚሰሩ ድርጅቶች ይገኙበታል። «በጋራ ለአፍሪቃ» በያመቱ እየመረጠ አንድ አገር ላይ ትኩረት ያደርጋል። በዚህ ዓመት ኢትዮጵያን መርጧል። በዚህም እዚያ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ይጎበኛሉ። ሰዎች ለሰዎች እንደሚታወቀው በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙት ትልልቅ ድርጅቶች አንዱ በመሆኑ «በጋራ ለአፍሪቃ» ከሚጎበኙት መካከል ነዉ። እናም እንደጥምረቱ ስያሜ ሁሉም በአንድ ላይ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪቃ የተሻለ ተግባር ያከናዉናሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።»

«በጋራ ለአፍሪቃ» ለተሰኘዉ የ20 ድርጅቶች ጥምረት እርዳታ ለማሰባሰብ በአባሳደርነት የሚያገለግሉት ጀርመናዊዉ የሙዚቃ ሰዉ ጀንትልማን እና በጀርመኑ የድምፃዉያን ዉድድር መድረክ ቮይስ ኦፍ ጀርመኒ ከሁለት ዓመት በፊት ያሸነፈችዉ የ21ዓመቷ አቀንቃኝ አይቪ ኩኤኖ ናቸው። ሣራ ለዶቼ ቬለ እንደገለጸችዉ ሁለቱ ከሰዎች ለሰዎች አባሳደርዋ ሣራ ኑሩ ጋር በመሆን በያዝነዉ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ያቀናሉ። የጉዞውም መርሐ-ግብር በጅምር ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን መመልከት ነው።

«አይቪ ኩኤኖና ጀንትልማን ሁለቱም የ«በጋራ ለአፍሪቃ» አባሳደሮች ናቸው። የጉዞው ዓላማም እኔ እንዳደረኩት ሰዎች ለሰዎች ለአለፉት ዓመታት ያከናወናቸዉንና አሁንም ምን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚያከናዉኑትን እንደ«ወርልድ ቪዥን» እና የመሳሰሉትን በርከት ያሉ ሥራዎች ይጎበኛሉ። እኔ እንደ ሰዎች ለሰዎች አምባሳደርነቴ በሚቀጥሉት ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ የእኛን ፕሮጀከቶች ወዳሉበት ወስጄ እንዲጎበኙ አደርጋለሁ። በዚህም እንደአምባሳደርነቴ ባለፉት ዓመታት ምን እንዳከናወነኩ ይመለከታኩ።»

ከሚጎበኙት የፕሮጀክት አካባቢ አንዱ ከአዲስ አበባ 125 ኪሎ ሜትር በሰሜን ምስራቅ የምትገኘው አሳግርት ከተማ ናት። በዚህ አካባቢ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከ1997ዓ,ም ጀምሮ ህብረተሰቡን በማገዝ ላይ ይገኛል። አሳግርት ለጉብኝት ለምን እንደተመረጠች ሣራ ስትገልፅ

«የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንመለከታለን፤ ከዚያም መካከል አሳግርት የሚገኘው የሰርቶ ማሳያ ፕሮጀክት አንዱ ነዉ። ፕሮጀክቱ ገበሬዎች ከብክለት በጸዳ መንገድ ለራሳቸዉ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጩበት ነዉ። ይህ ጉብኝት ለአይቪ ኩኤኖና ጀንትልማን ጥሩ ግንዛቤ በማግኘት በአጠቃላይ ሰዎች ለሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ምን እንደሚያከናውን ለመረዳት ያስችላቸዋል።»

ሙና ማሞ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic