የሰኞ ነሐሴ 6፣2019 ዓም የስፖርት ዝግጅት | ስፖርት | DW | 12.08.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የሰኞ ነሐሴ 6፣2019 ዓም የስፖርት ዝግጅት

የዛሬው ስፖርት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጀመረውን የእንግሊዝ ፕሬምየር ሊግን እና በዚህ ሳምንት የሚጀመረውን የጀርመኑን ቡንደስ ሊጋም ያስቃኘናል። «በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ዝግጅት ሴቶችን የሚያሳትፉ ውድድሮች ባለማዘጋጀት የቀረበበት ትችት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሃላፊ መልስም ተካቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:41

የሰኞ ነሐሴ 6፣2019 ዓም ስፖርት

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሁለት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ክለቦች ከሁለት አቻ የአፍሪቃ ሃገራት የእግር ኳስ ከለቦች ጋር ባካሄዱት ግጥሚያ አንደኛው ድል ሲቀዳጅ ሌላኛው ደግሞ ተሸንፏል።ያሸነፈው በባህርዳር ስታድዮም በአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከታንዛንያው አዛን የእግር ኳስ ክለብ ጋር የገጠመው ፋሲል ከነማ ሲሆን የተሸነፈው ደግሞ በኢኳቶሪያል ጊኒ ለአፍሪቃ እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ማጣሪያ ከኢኳቶሪያል ጊኒው «ከካኖ ስፖርት» ጋር  የገጠመው መቀሌ ሰባ እንደርታ ቡድን ነበር። የዛሬው ስፖርት ከሚያተኩርባቸው የእግር ኳስ ጨዋታዎች መካከል እነዚህ የእግር ኳስ ውድድሮች ይገኙበታል።ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጀመረውን የእንግሊዝ ፕሬምየር ሊግን እና በዚህ ሳምንት የሚጀመረውን የጀርመኑን ቡንደስ ሊጋም የዛሬው ስፖርት ያስቃኘናል።ከዚህ ሌላ «በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ዝግጅት ሴቶችን የሚያሳትፉ ውድድሮች ባለማዘጋጀት የቀረበበት ትችት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሃላፊ መልስ በዛሬው ስፖርት ተካተዋል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ 


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic