የሰንደቅ ዓላማ ፉክክር የወለደው የአዲስ አበባ ውጥረት  | ኢትዮጵያ | DW | 14.09.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰንደቅ ዓላማ ፉክክር የወለደው የአዲስ አበባ ውጥረት 

ከስደት የሚመለሱ ፖለቲከኞችን የመቀበሉ ሒደት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን የኃይል ሚዛን ማሳየት የሚፈልጉ ሰዎች የየራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ያንፀባርቃሉ የሚሉትን ባንዲራ በማውለብለብ እና ብዙ ሰው አደባባይ ላይ በማሳየት ተቀናቃኜ ነው ለሚሉት አካል የደጋፊዎቻቸውን ብዛት ለማሳየት ተፍጨርጭረዋል-ፍቃዱ ኃይሉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00

ሁለት ሰንደቅ ዓላማዎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ትርክቶች

ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉ የሰንደቅ ዓላማ ፉክክር የወለደውን አዲስ አበባ ውጥረት የፖለቲካ ትርክት ውድድር መገለጫ አድርጎ ይገልጸዋል። ለዲ ደብሊው በፃፈው የግል አስተያየት "ብሽሽቅ እና ፉክክሩ ነባር የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባሕል" እንደሆነ የገለጸው በፍቃዱ የአሁኑ ግን ከቅርብ ጊዜ ክስተቶች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ዕምነቱን ገልጿል። ከስደት የሚመለሱ ፖለቲከኞችን የመቀበሉ ሒደት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን የኃይል ሚዛን ማሳየት የሚፈልጉ ሰዎች የየራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ያንፀባርቃሉ የሚሉትን ባንዲራ በማውለብለብ እና ብዙ ሰው አደባባይ ላይ በማሳየት ተቀናቃኜ ነው ለሚሉት አካል የደጋፊዎቻቸውን ብዛት ለማሳየት ተፍጨርጭረዋል ብሏል። የሰንደቅ ዓላማዎቹ ውክልና፣ የፖለቲካ ኃይሎቹ ሚና እና የውጥረቱ ክረት ላይ ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉን አነጋግረነዋል።


እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic