የሰብዓዊ ርዳታ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ | ኢትዮጵያ | DW | 31.07.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰብዓዊ ርዳታ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ

የአውሮጳ ኅብረት ኮሚስዮን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ አስቸኳዩን የሰብዓዊ ርዳታ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ኮሚስዮኑ ለኢትዮጵያ አምስት፡ ለኤርትራ ደግሞ ስድስት ሚልዮን ዩር ርዳታ ለማቅረብ የወሰነው ከዓለም አቀፍ የርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የርዳታ ተማጽኖ ጥሪ ከቀረበለት በኋላ መሆኑን አርያም ተክሌ ያነጋገረቻቸው የኮሚስዮኑ የውጭ ግንኙነት ቃል አቀባይ ወይዘሮ ክርስቲያነ ሁማን ገልጸዋል።