የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዳርፉር | አፍሪቃ | DW | 16.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዳርፉር

የሱዳን መንግሥት ጦር ባለፈው ጥቅምት በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍለ ሃገር በዳርፉር ከተማ በርካታ ሴቶችና ህፃናትን ደፍሯል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች ባለፈው ሳምንት አጋልጧል ።

ድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ደረጃ መታየት ያለበትም ነው ሲል እሳስቧል ። HRW ያቀረበውን ይህን ዘገባ የሱዳን መንግሥት ሃሰት ሲል አስተባብሏል ።

መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ሂዩመን ራይትስ ዋች ባለፈው ረቡዕ ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው ሴቶችና ልጃገረዶቹ የተደፈሩት ባለፈው ጥቅምት 20 ፣ 2007 ዓም ዳርፉር በምትገኘዋ ታቢት በተባለችው መንደር ውስጥ ነው ።እንደ ዘገባው ታቢት አካባቢ የተሰማራው የሱዳን መንግስት ሠራዊት አንድ ወታደራችን ተገድሏል በሚል በወቅቱ ከ36

ሰዓትት በላይ የወሰደ ጥቃት ነበር የፈፀመው ። ድርጅቱ ከሁለት ወር ምርመራ በኋላ ባወጣው ባለ 48 ገፅ ዘገባው እንዳተተው ወታደሮቹ ጥቃቱን ያደረሱትም ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ ነበር ።የድርጅቱ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ አቶ ዳንኤል በቀለ።

በዚሁ የበቀል እርምጃ በግዳጅ የተደፈሩት ሴቶችና ልጃገረዶቹ ቁጥር ቢያንስ 221 ይሆናል እንደ ሂዩመን ራይትስ ዋች ።አቶ ዳንኤል እንዳሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ እንደተደረገ ጉዳዩን ለማጣራት የጠየቀው በአካባቢው የተሰማራው የአፍሪቃ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል በመጀመሪያ ተከልክሎ ኋላ ላይ ግን ተፈቅዶለት ወደ አካባቢው ቢሄድም በነፃነት መረጃ ማግኘት አለመቻሉን ነው አቶ ዳንኤል የተናገሩት ።

HRW በዚህ በጅምላ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ላይ ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያካሂድ

Human Rights Watch Logo Flash-Galerie

ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ በጎርጎሮሳዊው 2009 የሱዳኑን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽርን በዚሁ በዳርፉር በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀልና በዘር ማጥፋት የእሥር ማዘዣ ቆርጦባቸዋል ። ሆኖም የአፍሪቃ መንግሥታት ትዕዛዙን ለማስፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል ። አቶ ዳንኤል በተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤትም በኩል ይህ የፍትህ ጥያቄ በፖለቲካዊ አቋም ምክንያት መልስ አለማግኘቱ አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል ።

አቶ ዳንኤል እንደሚሉት በግዳጅ ለተደፈሩት የዳርፉር ሴቶችና ልጃገረዶቹ አስፈላጊውን የህክምናና የሥነ ልቡና እርዳታ ለማድረግም ሆነ ጉዳዩ እንዲመረመርና እንዲጣራ የሱዳን መንግሥት እንዲተባበር መደረግ ይኖርበታል ።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic